የናዚን መፈክር ያሰሙት የጀርመኑ ቀኝ ዘመም ፓለቲከኛ ተቀጡ
ፓለቲከኛው የናዚን መፈክር በማስተጋባት ተከሰው ጥፋተኛ ሲባሉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል

የናዚ ሀውልቶች፣ መፈክሮች እና በዚያ ዘመን የነበሩ ምልክቶች በሙሉ በጀርመን ህገወጥ ናቸው
የናዚን መፈክር ያሰሙት ታዋቂው የጀርመኑ ቀኝ ዘመም ፓለቲከኛ ተቀጡ።
አወዚጋባው የቀኝ ዘመም ፓለቲከኛ ብጆርን ሆይኬ የተከለከለውን የናዚ መፈክር በመጠቀማቸው የ16ሺ ዩሮ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ፓለቲከኛው የናዚን መፈክር በማስተጋባት ተከሰው ጥፋተኛ ሲባሉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
በምስራቅ ጀርመን ቱርንጊያ ግዛት የአልተርኔቲብ ሮፍ ጀርመኒ(ኤኤፍዲ) ፓርቲ መሪ የሆኑት ቀኝ ዘመሙ ሆይኬ በፈረንጆቹ 2023 የፓርቲ ስብሰባ ላይ "ሁሉም ለጀርመን" የሚል ቃል በመጠቀማቸው በሀል ከተማ በዳኞች ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
በቱርጊያ ግዛት ጌራ ከተማ በተካሄደው ዝግጅት ላይ "ሁሉም ለ" የሚል ሀረቅ በመጥራት የተሰበሰበው ህዝብ "ለጀርመን" እንዳሉ አነሳስቷል ተብሏል።
አዶልፍ ሂትለር ቁልፍ ሚና የተጫወተው የስተርማብቲለንግ ቡድን የሆነው ይህን መፈክር ጨምሮ የናዚ ሀውልቶች፣ መፈክሮች እና በዚያ ዘመን የነበሩ ምልክቶች ሙሉ በጀርመን ህገወጥ ናቸው።
ባለፈው ግንቦት ወር ይኸው ፍርድ ቤት ሆይኬ በፈረንጆቹ 2021 በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት መፈክሩን በመጠቀሙ የ13ሺ ዩሮ ቅጣት ጥሎበታል።
ህይኬ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ችሎት መክፈቻ ላይ ማንኛውም ሰው የሚጠቀምባቸው ቃላት የወንጀለኛ ድርጅት ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ክሱም መሰረተቢስ እንደሆነ ገልጿል።
በጀርመን ደህንነት ጽንፈኛ ተደርጎ የሚታየው ሆይኬ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እያወዛገበ ነው። በአንድ ወቅት በበርሊን ያለውን የሆሎካስት ወይም በናዚ ለተጨፈጨፉት አይሁዶች ማስታወሻነት የተሰራውን ሙዚየም "የነውር ማስታወሻ" ሲል የገለፈው ሆይኬ ሀገሪቱ የመዘከር ባህሏን "በ180 ዲግሪ መቀየር" እንዳለባት አሳስቦ ነበር።
ነገርግን በሆይኬ ላይ የተወሩት አሉባልታዎች በሆይኬ ታዋቂነት ላይ ጥላ አላጠሉበትም።