የሆሎካስት ተመራማሪዎች በስም ያልተመዘገቡ ሰለባዎችን ለመፈለግ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ መጠቀማቸውን ገለጹ
በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዶች በሂትለር ተጨፍጭፈዋል።
በያድ ቬሻም የዓለም ሆሎካስት ማስታወሻ ማዕከል ያሉ ሰራተኞች ኤአይ የታወቁ እና ያልታወቁ ሰለባዎችን ዝርዝር ሁኔታ እያጠኑ መሆናቸውን ተናግረዋል
የሀሎካስት ተመራማሪዎች በስም ያልተመዘገቡ ሰለባዎችን ለመፈለግ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ መጠቀማቸውን ገለጹ።
የእስራኤል ተመራማሪዎች ስማቸው ከመንግስት መዝገብ የጠፋውን በሆሎካስት (የዘር ጭፍጨፋ) የተገደሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዶችን ከክምር መዝገብ ውስጥ ለመፈለግ ፊታቸውን ወደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ማዞራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዶች በሂትለር ተጨፍጭፈዋል። በአይሁዶች ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት በመላው አለም ይዘክራል።
በእየሩሳሌም በሚገኘው ያድ ቬሻም የዓለም ሆሎካስት ማስታወሻ ማዕከል ያሉ ሰራተኞች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(ኤአይ) የሚሰራ ሶፍትዌር በማበልጸግ የታወቁ እና ያልታወቁ ሰለባዎችን ዝርዝር ሁኔታ እያጠኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ባለፉት አመታት በጎፈቃደኞች ጹህፎችን፣ ሰነዶችን፣ የመቃብር ላይ ጸለህፎችን እና ሌሎች መዝገቦችን በማየት የ4.9 ሚሊዮን ግለሰቦችን መረጃ አሰባስበዋል።
በማዕከሉ የሶፍትዌር ማበልጸግ ኃላፊ የሆኑት እሸር ፈክስሩመር "በሰው ልጅ ይህን መስራት ከባድ ነው፤ ሁሉንም መዳሰስ እና ዝርዝር ሁኔታን አለመሳት አይቻልም" ብለዋል።
አሁን ባለው ዘጠኝ ሚሊዮን መዝገብ ውስጥ ትልቅ ክፍተት አለ።
ናዚዎች "ሰዎችን ወስደው ከገደሉ በኋላ ጉድጓድ ውስጥ ይከቷቸዋል። ስለእነሱ የሚናገርላቸው ማንም አልነበረም"ይላሉ ፈክስሩመር።
በወቅቱ ግለሰቦችን ከእለታት፣ ከቤተሰብ አባላት እና ከሌሎች ዝርዝሮች ጋር ማያያዝ፣ ድግግሞሽን ማየት እና መረጃዎችን ማነጻጸር ከባድ ስራ ነበር።
በእንግሊዝኛ፣ በኸብሪው፣ በጀርመን፣ በሩሲያኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉ መዝገቦችን ለማገላበጥ ባለፉት ሁለት አመታት የበለፈጸገው ኤአይ በአሁኑ ወቅት ሙከራ እየተደረገበት ነው።
"ያ ቴክኖሎጂ በጣም ፈጣን ነው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ መረጃዎች በጥቂት ሰአታት ያጣራል፤ ውጤቱም በጣም ትክክል ነው" ሲሉ ፈክስሩመር ተናግረዋል።
ኤአይ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች በስም ከመለየት በሻገር ሙሉ ዝርዝር ለማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ሰራተኞቹ ከ30ሺ ማስረጃዎች የሶስት ሰአት ርዝማኔ ያለውን ቪዲዮ ጨምሮ በ400ዎቹ ላይ ሙከራ አካሂደዋል።