ልዩ አፍሪካዊ ልምድ በጋና
ጋና የፕላስቲክ ብክለትን ለመቀነስ ብሄራዊ የፕላስቲክ እርምጃ አጋርነት መስርታለች
ጋና የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን በየዓመቱ በዓመት የ5.4 በመቶ ጭማሪ አለው
የጋና ብሄራዊ የፕላስቲክ እርምጃ አጋርነት የፕላስቲክ ብክለትን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ የባለብዙ አካላት የትብብር መድረክ ነው።
በጋና ያለው ብክለት በዋናነት የሚፈጠረው በፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝና አስተዳደር ሲሆን፤ መሰብሰብ፣ ማዘጋጀት እና እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ባለመኖሩ ነው።
ሰፊ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ በቂ የገንዘብ አቅርቦት እና የድጋፍ ስልቶች አለመኖራቸው እነዚህን ተቋማት ለመገንባት እና ለመጠገን እንቅፋት ፈጥሯል።
በአካባቢው ነዋሪዎች የፕላስቲክ ቆሻሻን በአግባቡ አለመጣልም ለችግሩ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
ጋና በዓመት 0.84 ሚሊዮን ቶን የማዘጋጃ ቤት የፕላስቲክ ቆሻሻ ታመርታለች ተብሎ ይገመታል። ይህም በዓመት የ5.4 በመቶ ጭማሪ ነው።
የፕላስቲክ ቆሻሻ በየዓመቱ በ2.2 በመቶ የሚያድግ ሲሆን፤ ለዚህም የህዝብ ብዛት የመጀመሪያው ምክንያት ነው።
በተጨማሪም የነፍስ ወከፍ የፕላስቲክ ፍጆታ በየዓመቱ በ3.4 በመቶ ይጨምራል።
መንግስት፣ ኢንዱስትሪዎች እና ማህበረሰቡ የአካባቢ ተጽዕኖን ለመቅረፍ ቁርጠኝነት ቢኖራቸውም፤ ከ2020 እስከ 2040 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ የውሃ አካላት የሚለቀቀው የፕላስቲክ መጠን በ190 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ለዚህም ነው በሀገሪቱ አካባቢ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚንስቴር መሪነት የጋና ብሄራዊ የፕላስቲኮች እርምጃ አጋርነት መመስረትን ያስገደደው።
አጋርነቱ ለበርካታ ባለድርሻ አካላት ትብብር መድረክ እንዲሆን ነው የተመሰረተው።