ዓለም በታሪክ ውስጥ እጅግ ውስብስብ የሆነ የፕላስቲክ ቀውስ ገጥሟታል ተባለ
ከደቂቃዎች እስከ ሰዓታት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ምርቶች በአካባቢ ለብዙ መቶ ዓመታት ይቆያሉ
የፕላስቲክ ብክለት የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት እምብዛም ውጤታማ ባልሆነባቸው በእስያ እና አፍሪካ ሀገሮች ጎልቶ እንደሚታይ ተነግሯል
ከበርካታ ዓመታት በፊት ለፕላስቲክ አማራጭ ማግኘት ቀላል ያልነበረ ሲሆን አሁን ግን ሁኔታው ተቀይሯል።
ኩባንያዎች ለፕላስቲክ አማራጮች የሚሆኑ ምርቶች ላይ መስራት ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣ ይመስላል።
እንደ መስታወት፣ ብረት እና ወረቀት ባሉ ተለዋጭ እቃዎች ምርቶችን ለማሸግ የሚደረገው ጥረት ከፍ ቢልም የዓለም የፕላስቲክ ብክለት ችግር ግን ተባብሶ ቀጥሏል ተብሏል።
ለነጠላ ጥቅም የሚውሉ ፕላስቲኮች በየዓመቱ ከሚመረተው ፕላስቲክ 40 በመቶውን ይሸፍናሉ
እንደ ፕላስቲክ ከረጢቶች እና የምግብ መጠቅለያዎች ያሉ አብዛኛዎቹ ምርቶች ከደቂቃዎች እስከ ሰዓታት ያገለግላሉ። ነገር ግን በአካባቢ ለብዙ መቶ ዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ። ዋሽንግተን ፖስት ችግሩ የፕላስቲክ ቆሻሻ አስተዳደር ላይ ብሏል።
የፕላስቲክ ብክለት በጣም አሳሳቢ ከሆኑ የአካባቢ ጉዳዮች አንዱ ሆኗል። የሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶች በፍጥነት ማምረት እየጨመረ በመምጣቱ የዓለምን የመቆጣጠር አቅሙ እጅግ ፈትኗል ተብሏል።
የፕላስቲክ ብክለት የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓቶች እምብዛም ውጤታማ ባልሆነባቸው ወይም በማይገኝባቸው በእስያ እና አፍሪካ ሀገሮች ጎልቶ ይታያል። ነገር ግን የበለጸጉ ሀገራትም የተጣሉ ፕላስቲኮችንም በአግባቡ የመሰብሰብ ችግር አለባቸው።
የፕላስቲክ ምርት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። በፈረንጆቹ 1950 ከነበረበት 2.3 ሚሊዮን ቶን በ2015 ወደ 448 ሚሊዮን ቶን ይደርሳል። በ2050 ምርቱ በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።
በየዓመቱ ወደ 8 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የፕላስቲክ ቆሻሻ ወደ ባህር ዳርቻዎች ወደ ውቅያኖሶች ይገባል።
ፕላስቲኮች ለመበስበስ ቢያንስ 400 ዓመታት ይፈጅባቸዋል።