ኢጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም ላይ የሚደረገው ጨዋታ ለአፍሪካዊቷ ሀገር ወሳኝ ነው
ጋና ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ወሳኝ ጨዋታዋን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ታደርጋለች
በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ በፖርቹጋል 3 ለ 2 የተሸነፉት ጥቋቁሮቹ ከዋክብት ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።
ለእንግሊዙ ቶተንሃም የሚጫወተው ሰን ሁንግ ሚን ለደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ቡድን በ42 ጨዋታዎች 12 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ለኳታሩ አል ሳድ ክለብ የሚጫወተው የጋናው አንድሬ አየውም ለሀገሩ 111 ጨዋታዎች ተጫውቶ 24 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
ጋና እና ደቡብ ኮሪያ እስካሁን አራት ጊዜ ተጫውተው አንድ ጊዜ ደቡብ ኮሪያ አሸንፋለች፤ ቀሪዎቹ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
ሀገራቱ ለአምስተኛ ጊዜ የሚያደርጉት ጨዋታም ጋና የመጀመሪያውን ድሏን የምታስመዘግብበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
በምድብ 8 የመጀመሪያውን የአለም ዋንጫ ያዘጋጀችው ኡራጓይ ከፖርቹጋል ምሽት 4 ሰአት ላይ ትጫወታለች።
ከደቡብ ኮሪያ ነጥብ የተጋራችው ኡራጓይ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀገር ትፈተናለች ተብሎ ይጠበቃል።
ምሽት 4 ስአት ላይ ደግሞ ብራዚል ከስዊዘርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታም የዛሬው ተጠባቂ መርሃ ግብር ነው።