የጦር መሳሪያ የውጪ ንግዷ በግማሽ የቀነሰባት ሩሲያ በበኩሏ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ ተቀድማለች
የአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ንግድ ከ2019 እስከ 2023 ባሉት አምስት አመታት የ3 ነጥብ 3 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ።
የስቶኮልም የሰላም ጥናት ተቋም በአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ንግድ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸውን ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
አሜሪካ ከአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ንግድ 42 በመቶ ገደማውን በመያዝ ቀዳሚዋ ናት፤ የጦር መሳሪያ ሽያጯ በ17 በመቶ ያደገላት ዋሽንግተን ለ107 ሀገራት መሳሪያዎቿን አቅርባለች።
የአውሮፓ ሀገራት ባለፉት አምስት አመታት ካስገቡት የጦር መሳሪያ 55 በመቶው ከአሜሪካ የተገዛ ነው ይላል የጥናት ተቋሙ።
ከአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ሲሶ የሚሆን ድርሻ ያላቸው የአውሮፓ ሀገራት ከግዥ ባለፈ በሽያጩ ረገድ ያላቸው አቅም እያደገ መሄዱም ተመላክቷል።
አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት ከአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ንግድ 72 በመቶውን ይሸፍናሉ።
ከአሜሪካ በመከተል ሁለተኛ ደረጃ ይዛ የቆየችው ሩሲያ የጦር መሳሪያ የወጪ ንግዷ በግማሽ ቀንሷል ብሏል የስቶኮልም የሰላም ጥናት ተቋም።
በ2029 ለ31 ሀገራት የጦር መሳሪያዎችን የሸጠችው ሞስኮ በ2023 ለ12 ብቻ ሀገራት ነው የሸጠችው።
ይህም ከአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ያላትን ድርሻ ዝቅ አድርጎት ለመጀመሪያ ጊዜ ደረጃዋን በፈረንሳይ እንድትነጠቅ ማስገደዱ ተገልጿል።
በአለማቀፉ የጦር መሳሪያ ንግድ የሀገራት ድርሻን ይመልከቱ፦