ድራጎን ፋየር የተሰኘው ይህ የጦር መሳሪያ ከለንደን ወደ ሞስኮ በ9 ደቂቃ መግባት እንደሚችል ተገልጿል
ብሪታንያ በ10 ፓውንድ የሚገዛ የጦር መሳሪያ መስራቷ ተገለጸ፡፡
የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ከሆነ 10 ፓውንድ የሚያወጣ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ መስራቱን አስታውቋል፡፡
የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ከብሪታንያ የጦር መሳሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በቅንጅት ሰራው የተባለው ይህ የጦር መሳሪያ ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤል እና ድሮኖችን መምታት ይችላል ተብሏል፡፡
የብሪታንያ መከላከያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቤተ ሙከራ ከሊኦናርዶ እና ኪነትክ ከተሰኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር በተሰራ ቅንጅት የተሰራው ይህ ድራጎን ፋየር ጦር መሳሪያ በአጠቃላይ ምርቱን ለመጨረስ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት 355 ሺህ ወታደሮችን እንዳጣች ብሪታንያ ገለጸች
ይሁንና ድራጎን ፋየር የተሰኘውን የጦር መሳሪያ ለገበያ የሚቀርበው በ10 ፓውንድ ዋጋ ነው የተባለ ሲሆን የጦር መርከቦችን ለማስመጥ እና ለመምታት ፣ የጦር አውሮፕላኖችን ለመምታት እና የሩሲያን ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤሎችን ለመምታት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡
በዋጋው ርካሽ የሆነው እና በአገልግሎቱ ተፈላጊ የሆነው ይህ የጦር መሳሪያ ከለንደን ወደ ሞስኮ ለመጓዝ ዘጠኝ ደቂቃዎች ብቻ ይፈጁበታልም ተብሏል፡፡
ብሪታንያ የዚህን ጦር መሳሪያ ውጤታማነት በቅርቡ ሞክራው ስኬታማ ሆኗል የተባለ ሲሆን በአንድ ኪሎ ሜትር ውስጥ ለች ትንሽዬ ሳንቲምን መምታት እንደሚችል መረጋገጡ ተገልጿል፡፡
ይሁንና ብሪታንያ ስለዚህ አነጋጋሪ የጦር መሳሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከማውጣት ተቆጥባለች፡፡