ዓለምን ደጋግመው ማውደም ይችላሉ የሚባሉት የሩሲያ ኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ቁልፍ በማን እጅ ነው?
ሩሲያ በኑክሌር አረር ብዛት ከዓለም ቀዳሚዋ ሀገር ናት
ሩሲያ የኑክሌር አረሯን መቼ እንደምትጠቀም ሕግ ማውጣቷ ይታወሳል
የሩሲያ ኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ቁልፍ በማን እጅ ነው?
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ሩሲያ ለኑክሌር ጦርነት ዝግጁ መሆኗን መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ሩሲያ 5580 የኑክሌር አረር በመያዝ ከየትኛውም የዓለማችን ሀገራት በላይ አውዳሚ የጦር መሳሪያ የታጠቀች ሀገር ስትሆን ተጨማሪ ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያዎችን በማምረት ላይ መሆኗን የአሜሪካ ሳይቲስቶች ፌዴሬሽን ሪፖርት ያስረዳል፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ሩሲያ በየጊዜው የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን እያዘመነች የመጣች ሲሆን በአጭር እና ረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ላይም ተገጥመዋልም ተብሏል፡፡
እነዚህ የኑክሌር አረሮች ከአየር፣ ከምድር እና ከባህር ላይ እንዲተኮሱ ተደርገው ተዘጋጅተዋል የተባለ ሲሆን የጦር መሳሪያዎቹ ቢተኮሱ ዓለምን ብዙ ጊዜ ደጋግመው ማውደም የሚችሉ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
ሩሲያ እነዚህን አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች መቼ፣ ማን እና እንዴት ይተኮሳሉ የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስ የኑክሌር ጦር መሳሪያ መመሪያ አውጥታለች፡፡
በዚህ መመሪያ መሰረት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቹ ከየትኛውም ቦታ ሆነው በማንኛውም ጊዜ እንዲተኮሱ የመጨረሻ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ይቻላል ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የነዚህን ኑክሌር አረር መሳሪያዎች ቁልፍ እንደያዙ ሲገለጽ ፕሬዝዳንቱ ባሉበት ሆነው የጦር መሳሪያዎቹ እንዲተኮሱ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉባቸው ሁለት ቁልፎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡
አንደኛው ቁልፍ የኑክሌር አረሮቹ በተቀመጡባቸው ቦታዎች ሁሉ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የጦር መሳሪያዎቹ እንዲተኮሱ ሚስጢራዊ ትዕዛዝ የሚያስተላልፉበት ነው፡፡
ሩሲያ ከአጋሮቿ ጋር ወታደራዊ ልምምድ እንደምታካሄድ አስታወቀች
የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሼጉ መሳሪያዎቹ የት እንዳሉ እና እንዲተኮሱ ትዕዛዝ የማስተላለፍ ሀላፊነት እንደተሰጣቸውም ተገልጿል፡፡
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሶቭየት ህብረት 40 ሺህ ኑክሌር አረር የነበራት ሲሆን አሜሪካ 30 ሺህ ያህል ነበራት፡፡
ዓለምን ከጅምላ ጨራሽ ጦር መሳሪያዎች ለመታደግ ሲባልም ሁለቱ ሀገራት ባደረጉት ስምምነት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን ቁጥር ቀንሰዋል፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ሩሲያ ከዚህ ስምምነት መውጣቷን ይፋ ያደረገች ሲሆን ተጨማሪ የኑክሌር አረር ጦር መሳሪያ በማምረት ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡