የ2.7 ትሪሊየን ዶላር ዓመታዊ ኪሳራ
በዚህ ሳምንት ዓለም አቀፍ የአካባቢ አስተባባሪ ሰባተኛ ስብሰባውን በቫንኩቨር ካናዳ ተደርጓል
በ30 ዓመታት ጉዞው 23 ቢሊየን ዶላር የአካባቢ ጥበቃ ገንዘብ መቅረብ ችሏል
በዚህ ሳምንት ዓለም አቀፍ የአካባቢ አስተባባሪ ሰባተኛ ስብሰባውን በቫንኩቨር ካናዳ ተደርጓል።
ታላቅ የአካባቢ መድረክ የሆነው ስብሰባው፤ የ185 ሀገራት ተወካዮች፣ የኢንዱስትሪ ሚንስትሮች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም ከነባር ህዝቦች፣ ወጣቶችና ሴቶች ልዑኮች ተሳትፈውበታል።
ዓለም አቀፉ የአካባቢ አስተባባሪ የብዝሀ ህይወት ጉዳቶችን፣ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል፣ ብክለትን መቀነስና መሬትንና ውቅያኖስን ለመጠበቅ የሚሰራ ገንዘብ አቅራቢያ ድርጅት ነው።
- የአየር ንብረት ለውጥ ከ4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የኢኮኖሚ ኪሳራ ማድረሱ ተገለጸ
- የአየር ንብረት ለውጥ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ በ10 ሚሊየን ሰዎችን ሊያፈናቅል ይችላል- የዓለም ባንክ
በጎርጎሮሳዊያኑ 1991 የተመሰረተው ድርጅቱ፤ በ30 ዓመታት ጉዞው 23 ቢሊዮን ዶላር የአካባቢ ጥበቃ ገንዘብ መቅረብ ችሏል።
እንደ ድርጅቱ ይፋዊ ድረ ገጽ መረጃ ከሆነ ከአምስት ሽህ በላይ ሀገራዊና ቀጣናዊ ፕሮጀክቶችን ተግብሯል።
ለአካባቢ የገንዘብ አቅርቦት ብቁ በሆኑ በሁሉም ሀገራት 94 በመቶ የሚሰራው ድርጅቱ፤ በታዳጊ ሀገራት፣ በኢኮኖሚ እየተሸጋገሩ ባሉ ሀገራትና በትናንሽ ደሴቶች ይሰራል።
በአጠቃላይ የብዝሀ ህይወት መመናመን በ2030 ከዓለም ጠቅላላ ምርት የ2.7 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ኪሳራ እንደሚደርስ የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ገልጿል።
ነገር ግን አሁንም ተስፋ አለ። በ2022 የወጣው ስልታዊና ዓለም አቀፋዊ ፍኖተ ካርታ ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ብዝሀ ህይወትን መመለስና በዘላቂነት ማስተዳደር ያስችላል።