ከባህር ስር በተዘረጉ የኢንተርኔት ኬብሎች ላይ ባጋጠመው ብልሽት ምክንያት በበርካታ የምዕራብ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት ኢንተርኔት መቋረጡን ኢንተርኔት ኦብዘርቫቶሪይ ኔት ብሎክስ ገልጿል
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እንተርርኔት መቋረጥ እንዳጋጠማቸው ኔት ብሎክስ አስታውቋል።
ከባህር ስር በተዘረጉ የኢንተርኔት መስመሮች ወይም ኬብሎች ላይ ባጋጠመው ብልሽት ምክንያት በትናትናው እለት በበርካታ የምዕራብ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት ኢንተርኔት መቋረጡን ኢንተርኔት ኦብዘርቫቶሪይ ኔት ብሎክስ ገልጿል።
ኬብሉ በምን ምክንያት እንደተበላሸ እስካሁን ግልጽ አልተደረገም።
የአፍሪካ ከባህር ስር ያሉ ኬብሎች ተቆጣጣሪ(ሲኮም) እንዳረጋገጠው የምዕራብ አፍሪካ ኬብል ሲስተም መበላሸቱን እና በዚያ መስመር ላይ የነበሩ ደንበኞች ሲኮም ከሚጠቀምበት ኢኩያኖ ኬብል ጋር እንዲገናኙ መደረጉን አረጋግጧል።
ሲኮም እንደገለጸው አንዱ ኬብል ሲበላሽ ወደ ሌላ የማዛወሩ ስራ አውቶማቲክ ወይም ወዳያውኑ የሚደረግ ነው።
ኮትዲቯር፣ ላይቤሪያ፣ ቤኒን፣ጋና እና ቡርኪናፋሶ ከፍተኛ ችግር እንዳጋጠማቸው የኔትብሎክ መረጃ ያመለክታል።
የኢንተርኔት ኩባንያ የሆነው ክላውድፍሌር በኤክስ ገጹ እንደጻፈው ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ኮትዲቯር፣ ጋና፣ ቤኒን እና ኒጀር ከፍተኛ የኢንተርኔት መቋረጥ አጋጥሟቸዋል።
"ከሰሜን እስከ ደቡብ አፍሪካ ያለው የኢንተርኔት መቆራረጥ የሰአት ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል" ብሏል ክላውድ ፍሌር።
የደቡብ አፍሪካው ቴሌኮም ኦፕሬተር ቮዳኮምም በባህር ስር ያሉ ኢንተርኔት ኬብሎች መበላሸት በኢንተርኔት ሰጭ ኩባኔያዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል ብለዋል።