በሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት ቀዳሚ የሆኑ የዓለም ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
አረብ ኤምሬትስ 286.24 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በሞባይል የኢንተርኔት ፍጥነት ቀዳሚውን ደረጃን ይዛለች
ኢትዮጵያ በየካቲት ወር አንድ ደረጃን ማሻሻል መቻሏ ተመላክቷል
የስፒድ ቴስት ጎላባል በሀገራት ያለውን የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት በሜጋ ባይት በሰከንድ እና በዓለም ላይ ያላቸውን ደረጃ ይፋ አድርጓል።
በሪፖርቱ መሰረትም አረብ ኤምሬትስ በጥርና በየካቲት ወር 2024 በሞባይል የኢንተርኔት ፍጥነት ያለባት ሀገር በመባል ከዓለም ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች።
ሀገሪቱ 268.24 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 26.3 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት ቀዳሚ ሆናለች።
ኳታር በሞባይል ኢነተርኔት ፍጥነት ከዓለም 2ኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን፤ ሀገሪቱ 284.21 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 27.7 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት ሁለተኛ ሆናለች።
ተከታዩ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኩዌት ስትሆን፤ ሀገሪቱ 216..96 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 23.73 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት ሶስተኛ ሆናለች።
ደቡብ ኮሪያም 173.95 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 18.75 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አራተኛ ደረጃን ይዛለች።
5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ዴንማርክ ስትሆን፤ 157.94 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 20.77 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
6ኛ ቻይና ስትሆን፤ 144.85 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 27.25 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
7ኛ ኖርዌይ ስትሆን፤ 141.40 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 19.93 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
8ኛ አይስላንድ፤ 136.91 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 17.90 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
9ኛ ኔዘርላንድስ 134.15 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 19.14 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
10ኛ ሳዑዲ አረቢያ 125.19 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 15.10 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
አሜሪካ በዝርዝሩ ላይ 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ 122.74 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 10.02 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።
ኢትዮጵያም በየካቲት ወር አንድ ደረጃን በማሻሻል ከዓለም 83ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ 29.49 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በማውረድ እና 17.33 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመጫን በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ፍጥነት አላት።