የሒሳብ ትምህርት ዉጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ
ዋና መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገው ዓለም አቀፉ ተቋም የዓለም ሀገራት ሒሳብ እና ሳይንስ ትምህርት ውጤት ይፋ አድርጓል
በሒሳብ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግቡ የነበሩ የአሜሪካ፣ ጀርመን እና ኔዘርላንድ ተማሪዎች የውጤት ማሽቆልቆል አጋጥሟቸዋል ተብሏል
የሒሳብ ትምህርት ዉጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ፡፡
ዋና መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት በየዓመቱ የሒሳን እና ሳይንስ ትምህርት ፈተናዎችን ይሰጣል፡፡
ድርጅቱ በ2022 የተሰጡ ዓለም አቀፍ ፈተና ውጤቶችን ይፋ ያደረገ ሲሆን 700 ሺህ የዓለማችን ተማሪዎች ፈተናውን እንደወሰዱ ተገልጿል፡፡
በ81 የዓለማችን ሀገራት ያሉ ታዳጊዎች የሒሳብ፣ ሳይንስ እና ማንበብ ፈተናዎችን የወሰዱ ሲሆን የሒሳብ ፈተና ውጤት በበርካታ ሀገራት ዝቅ እንዳለ ድርጅቱ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
የነገ የዓለማችንን መሪዎች እና ተመራማሪዎችን ለመለየት የሚሰጠው ይህ ፈተና ከዚህ በፊት ጥሩ ውጤት ያስመዘግቡ የነበሩ ሀገራት ዘንድሮ ውጤት እንዳልቀናቸው ተገልጿል፡፡
ፈተናው ላይ ከተቀመጡ አራት ተማሪዎች መካከል አንዱ በሒሳብ ዝቅተኛ ውጤት አምጥቷል የተባለ ሲሆን በተለይም የሲንጋፖር ተማሪዎች የዓለማችን ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል ተብሏል፡፡
ጃፓን፣ ኢስቲኒያ፣ ቻይና፣ ካናዳ እና ደቡብ ኮሪያ በሒሳብ እና ሳይንስ ትምህርቶች የተሸለ ውጤት ያስመዘገቡ ተጨማሪ ሀገራት ናቸው፡፡
ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ኔዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ፖላንድ በሒሳብ ትምህረት ዝቅተኛ ውጤት እንዳስመዘገቡ ተገልጿል፡፡
59 ጊዜ የመንጃ ፍቃድ ፈተና የወደቀው ተማሪ አለፈ
ከአፍሪካ በብቸኝነት ሞሮኮ ተማሪዎቿን ያስፈተነች ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው ውጤት ጋር ተቀራራቢ ውጤት እንዳስመዘገቡ ይሄው ተቋም በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋት፣ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማዋል እና የመምህራን ብቃት መቀነስ ለተማሪዎች ውጤት መቀነስ ዋነኞቹ ምክንቶች ሆነው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡
ጥናቱን የሰራው ኦሲድ የተሰኘው ተቋም ከፈረንጆቹ 2000 ሺህ ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ 15 ዓመት የሆናቸው የዓለማችንን ተማሪዎች የሒሳብ፣ ሳይንስ እና ማንበብ አቅማቸውን ለመለካት ፈተና በመስጠት ይታወቃል፡፡
የዚህ ተቋም የፈተና ውጤት ተመድን ጨምሮ የዓለም ሀገራት የትምህርት ጥራታቸውን ለመለካት ይጠቀሙበታል፡፡