59 ጊዜ የመንጃ ፍቃድ ፈተና የወደቀው ተማሪ አለፈ
በእንግሊዝ የመንጃ ፈቃድ 'ቴዎሪ' ፈተና 59 ጊዜ ከወደቀ በኋላ ማለፍ የቻለው ተማሪ ላሳየው "ቁርጠኝነት" አድናቆት ተችሮታል
ይህ ተማሪ በሬዲች፣ ወርስተርሻየር ማዕከል ፈተናውን ለማለፍ 60 ሰአታት እና 1400 ዩሮ ፈጅቶበታል
የመንጃ ፍቃድ 'ቲዎሪ' ፈተና 59 ጊዜ ከወደቀ በኋላ ያለፈው ተማሪ አድናቆትን አተረፈ።
በእንግሊዝ የመንጃ ፈቃድ 'ቴዎሪ' ፈተና 59 ጊዜ ከወደቀ በኋላ ማለፍ የቻለው ተማሪ ላሳየው "ቁርጠኝነት" አድናቆት ተችሮታል።
ይህ ተማሪ በሬዲች፣ ወርስተርሻየር ማዕከል ፈተናውን ለማለፍ 60 ሰአታት እና 1400 ዩሮ እንደፈጀበት ስካይ ኒውስ አስነብቧል።
የግለሰቡ ማንነት በሚስጥር የተያዘ ቢሆንም ያለመሰልቸት ያደረገውን ሙከራ እና ያገኘውን ውጤት ኤኤ የተባለው የመንጃ ፈቃድ ትምህርት ቤት ይፋ አድርጎታል።
በእንግሊዝ ተማሪዎች የተግባር ፈተና ከመፈተናቸው በፊት የ'ቲዎሪ' ፈተና መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።እንደዘገባው ከሆነ ተማሪዎች ከሚቀርቡላቸው 50 የምርጫ ጥያቄዎች 43ቱን በትክክል መመለስ አለባቸው።
ከምርጫ ጥያቄዎች በተጨማሪ የአደጋ ምልክቶችን ያካተተ የቪዲዮ ክሊፖች ይቀርቡላቸዋል።
ከአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ስታንዳርድ ኤጄንሲ የተገኘው የዚህ አመት መረጃ እንደሚያመለክተው የመንጃ ፈቃድ ፈተና የማለፍ ምጥነት ቀንሷል። ተማሪዎች የሚወድቁበት መጠን እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኤጀንሲው ለ58ኛ፣ ለ56ኛ እና ለ54ኛ ጊዜ የቲዎሪ ፈተና ከወደቁ በኋላ ማለፍ የቻሉ ሌሎች ተማሪዎችም አሉ ብሏል።
ተማሪዎች ከወደቁ የ23 ዩሮ ፈተና ለመፈተን ሶስት ቀናት መጠበቅ ይኖርባቸዋል። በድጋሚ ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ከሆነ እስከሚያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ።
የትራንስፖርት ዲፖርትመን ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ የቲዎሪ ፈተና የማለፍ ምጥነት በ2007/08 ከነበረበት 65 በመቶ በ2022/23 ወደ 44 በመቶ ዝቅ ብሏል።