የወርቅ አምራቾች እና ሻጮች ወርቁን በሸጡበት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ ይፈጸምላቸዋል
ብሔራዊ ባንክ ከምንዛሬ ስርአት ለውጥ በኋላ ወርቅ የሚገዛው በአለምአቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በድረ ገጹ ይፋ እያደረገ ይገኛል።
በእየለቱ በምን ያህል የውጭ ምንዛሬ ወርቅ እንደሚገዛ በጽረ-ገጹ ይፋ እንደሚያደርግ የገለጸው ባንኩ፣የዛሬ የወርቅ መግዣ ዋጋን ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ባለ 24 ካራት 1 ግራም ወርቅ 78.1625 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 381 ብር እየገዛ መሆኑን አስታውቋል።
ባለ 23 ካራት 1 ግራም ወርቅ 74.9057የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 32.7314 ብር እየገዛ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመለክታል።
ባለ 22 ካራት 1 ግራም ወርቅ 71.6489 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 7 ሺህ 683.4822 ብር እየገዛ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።
ባለ 21 ካራት 1 ግራም ወርቅ 68.3922 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 7 ሺህ 334.233 ብር እየገዛ ይገኛል።
ባለ 20 ካራት 1 ግራም ወርቅ 65.1354የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 6 ሺህ 984.9838 ብር እየገዛ መሆኑን ነው ባኩ በድረ ገጹ ያወጣው መረጃ ያሚያመለክተው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባክ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫው የወርቅ አምራቾች እና ሻጮች ወርቁን በሸጡበት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ ይፈጸምላቸዋል ማለቱ ይታወሳል።
ወርቅን በብቸኝነት የሚገዛው ብሔራዊ ባንክ ነው።