በወርቅና በውድ ግብዓቶች እድሳት እየተደረገለት ያለው ሰሳዑዲው ከዓባ
በእዳሳቱ ላይ ከ120 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል
በከዓባ ላይ የጥገናና የእድሳት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል
የሳዑዲ አረቢያ የሁለቱ ቅዱስ መስጊዶች አስተዳደር የጥገና እና የንብረት አስተዳደር ክፍል የከዓባ ግንብ እድሳት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
በጥገናውም የከዓባ ልብስን ለመስቀል የሚያስችሉ 54 ወርቃማ ቀለበቶች ማስተካከል፣ በካዓባው እና በየመን ጥግ ዙሪያ ያለውን የሻዛርዋን እብነበረድ ሙሉ ምርመራን ያካትታል።
የእድሳት ስራውን በበላይነት የሚመሩት ኢንጂነር ሱልጣን አልቁራሺ፤ እየተካሄደ ያለው ጥገና በወጣው መርሃ ግብር መሰረት መሆኑን እና ከዓባውን ከጉዳት ለመጠበቅ ያለመ ነው ብለዋል።
በእድሳቱ የከዓባውን ሽፋን ቀለበቶች ማስተካከል እንዲሁም ሌሎች የማስተካል እና የማጽዳት ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
ከቁርዓን የተወሰዱ ጥቅሶች ያሉበት የከዓባው ልብስም የሚቀየር ሲሆን፤ በቅዳሜ እለት የከዓባው ልባስ እንዲወርድ በማድረግ በአዲሱ አንደሚተካመወ አስታውቀዋል።
ኪስዋ በተባለ ኢንደስትሪ የሚዘጋጀው የከዓባው ልብስ 670 ኪሎ ግራም ጥቁር ሲልክ፣ 120 ኪሎ ግም ወርቅ እና 100 ኪሎ ግራም በብር ገመድ ነው የሚዘጋጀው።
የአንዱ የከዓባ ልብስ ዋጋም 17 ሚሊየን የሳዑዲ ሪያል አሊያም 4.53 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያወጣም ነው የተነገረው።
አሮጌው ኪስዋ በትናንሽ ቁርጥራጮች ተቆርጦ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የሚሰጥ መሆኑም ተነግሯል።