ጎግል "ሚስጥር" ለመደበቅ 26 ቢሊዮን ዶላር መክፈሉ ተነገረ
ጉግሉ በዋሽንግተን በአስርት አመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ እምነት የማጉደል ክስ ቀርቦበታል
ጉግል በስልክ እና በኮሞፒውተር ላይ ተጠቃሚዎቹ እንዲመለከቱት የማይፈልገው 'ሴቲንግ' አለ ተብሏል
ጎግል "ሚስጥር" ለመደበቅ 26 ቢሊዮን ዶላር መክፈሉ ተነገረ።
በዋሽንግተን ፖስት የታተመው ሪፖርት እንደሚያመለክተው ቀዳሚ ሰርች ኢንጂን ወይም መረጃ መፈለጊያ ለመሆን እየጣረ ያለው ጉግልን ችግሮች አጋጥመውታል።
ጎግል በስልክ እና በኮሞፒውተር ላይ ተጠቃሚዎቹ እንዲመለከቱት የማይፈልገው 'ሴቲንግ' አለ ተብሏል።
ጉግል በፈረንጆቹ 2ዐ21 ብቻ በአፕል፣ በሳምሰንግ እና በሌሎች ላይ ይህን 'ሴቲንግ' ለመደበቅ 26.3 ቢሊዮን ዶላር አውጥቷል። ይህ 'ሴቲንግ' ማን ምን እየፈለገ እንደሆነ፣ የት አካባቢ እንዳለ እና ምን አይነት ማስታወቂያዎች እየመጡለት እንደሆነ ለማወቅ የሚያስችል መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል።
ይህ ጉዳይ የግዙፉን የመረጃ መፈለጊያ ዝና ብቻ ሳይሆን ለአፕል፣ለሳምሰንግ እና ለሌሎች ስልክ አምራች ኩባንያዎች የተሰጠውን እምነት ሊሸረሽረው ይችላል ተብሏል።
ጎግል ላይ የቀረበው ክስ
ጎግል ኩባንያ በዋሽንግተን በአስርት አመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ እምነት የማጉደል ክስ ቀርቦበታል።
የአሜሪካ መንግስት ጉግል ላይ ያቀረበው ክስ ለስልክ እና ኮምፒውር አምራቾች ህገወጥ ክፍያ በመፈጸም ሰዎች ሌላ ሰርች ኢንጂን ወይም የመረጃ መፈለጊያ እንዳይጠቀሙ አድርጓል የሚል ነው።
ጎግል ከበርካታ ተጠቃሚዎች መረጃ ስለሚያገኝ የተሻለ የፍላጋ ውጤት በማስገኘት ዝናን አትርፏል። እንዲሪፖርቱ ከሆነ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሰዎች ስራ ስለሚበዛባቸው ይህን 'ሴቲንግ' እና 'ፕራይቬሲ' ዳታ አያዩትም ብለው ያስባሉ።