በመካከላቸው የ37 ዓመት የእድሜ ልዩነት ያለው ባልና ሚስት “ሴት ልጅ ልንወልድ ነው” አሉ
የ63 ዓመት አዛውንት ሚስት እና የ26 ዓመቱ ወጣት ባል የልጃቸውን ጾታ የማብሰሪያ ድግስ አዘጋጅተዋል
የ63 ዓመቷ ሚስት ከዚህ በፊት 7 ልጆች ያላት ሲሆን፤ 17 የልጅ ልጆችንም አይታለች
በመካከላቸው የ37 ዓመት የእድሜ ልዩነት ያለው ባልና ሚስት “ሴት ልጅ ልንወልድ” ነው በማለት በቤታው ድግስ ማዘጋጀታቸው ተሰምቷል።
የ63 ዓመቷ አዛውንት እና የ26 አመት እድሜ ያለው ፍቅረኛዋ የመጀመሪያ ልጃቸው መጸነሱን ተከትሎ የፆታ ማሳወቂያ ድግስ ማካሄዳቸው ነው የተነገረው።
የ63 ዓመቷ ሚስት ቼርሊ ገሪጎር የ7 ልጆች እናት ስትሆን፤ 17 የልጅ ልጆችንም አይታልች፤ ቁራን ማክኬይን ከተባው የአሁኑ ወጣት በሏ ጋርም ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘችው በፈረንጆቹ 2012 ላይ ሲሆን፤ ቁራን በወቅቱ የ15 ዓመት ታዳጊ ነበር።
ለዓመታት በፍቅር የቆዩት ሁለቱ ጥንዶች በፈረንጆቹ 2021 ላይ በትዳር የተጣመሩ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ዓመት ላይ ልጅ ለመውለድ ማሰባቸውን እና ይህም ቼርሊ በተፈጥሮ መንግድ መውለድ ስለማትችል በማህጸን ኪራይ ለመውለድ ማቀዳቸውን አስታውቃው ነበር።
ጥንዶቹ ከሰሞኑ ደግሞ ልጃቸው መጸነሱን እና የልጃቸውን ጾታ ማሳወቅን ለማክብር ብለው ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ድግስ ማዘጋጀታቸው ነው የተነገረው።
በቲክቶክ ላይ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን ባገኘው ቪዲዮ ላይም ላይ፣ ቼርሊ ሮዝ ቀሚስ እና 'እናት ልትሆን ነው'' የሚል ጽሁፍ ያለበት ሪቫን ለብሳ ታይታለች።
የልጃቸው ጾታ ሴት መሆኑን መታወቁን ተከትሎ የ17 የልጅ ልጆችን ያየችው የ63 ዓመቷ ቼርሊ የ26ዓመቱ ባሏን አቅፋ እየዘለለች ስትጨፍርም ታይቷል።
ቼርሊ እና ቁራን እንዴት እንደተገናኙ ሲናገሩም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በፈረንጆቹ 2012 ላይ ዲያሪ ኩዊን በተባለ ምግብ ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ ሲሆን፤ በወቅቱም ቁራን የ15 ዓመት ታዳጊ፤ ቼርሊ ገድሞ የ52 ዓመት እድሜ ያላት ጎልመሳ ነበሩ።
በመሃል ተጠፋፍተው የነበሩት ጥንዶቹ በ2020 ላይ ድጋሚ ቼርሊ በገንዘብ ያዥበት ተቀጥራ በምትሰራበት ድርጅት ውስጥ ዳግም እንደተገናኙም ተናግረዋል።
ጥንዶቹ በ2021 ላይ መጋባታቸውንም ነው የሚናገሩት።
የ63 ዓመቷ ቼርሊ 7 ልጆች እና 17 የልጅ ልጆች ያላት ሲሆን፤ ነገር ግን ከቁራን ጋር የራሳቸው ልጅ እንዲኖራቸው ይመኙ እንደነበረ ተናግረዋል።
ቼርሊ የእድሜ ልዩነታቸው ስትናገር፣ “ቁርኣን እስካለ ድረስ የሚያሳስበኝ ነገር የለም፤ በእሱ ላይ እምነት አለኝ” ብላለች።
“እኔ ባለኖር እንኳ እሱ ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል፤ እሱ ታላቅ አባት ይሆናል፤ ኃላፊነት የሚሰማው አዋቂ ነው፤ ልጃችንን ማሳደግ እንደሚችል እና በጣም ጥሩ እንደሚያደርገው እምነት አለኝ ብላለች” ቼርሊ ስለ ወደፊቱ ስትናገርም።
“ቤተሰባችን ልጆች ለመውለድ ያደረግነውን ውሳኔ በጣም ይደግፋሉ” ያለችው ቼርሊ፤ “መጀመሪያ ላይ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ጥርጣሬዎች ነበራቸው” ብላለች።
ቁርኣን ከዚህ ቀደም ስለ ትዳራቸው በሰጠው አስተያየት “በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉ ሰዎች ለኛ ብዙ ጥላቻ አላቸው፤ ከአያቴ ጋር እንደተጋባው አድርገውም ያስባሉ” ብሏል።
“እኔ አያቴን አላገባሁም፤ እሷ ከአያቴ በእድሜ ታንሳልች፤ እኛ ከሌሎች ጥንዶች በምንም አንለይም፤ ምክንያቱም ፍቅር ፍቅር ነው” ሲልም ተናግሯል።