የውድድሩ አሸናፊዎች የ200 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል
23ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
ውድድሩ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች፣ አምባሳደሮች ፣ ተጋባዥ አትሌቶች እንዲሁም 45 ሺህ ዜጎች የተሳተፉበት እንደነበር ተገልጿል።
በዚህ አመት ውድድር አረንጓዴ እና ቢጫ ቀለም ያላቸው ቲሸርቶች ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን፥ አረንጓዴ ቲሸርት ውድድሩን ከ1 ስአት በፊት ማጠናቀቅ የሚችሉት ለብሰዋል።
በውድድሩ ላይ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረስቡ አባላትም ተሳትፈዋል።
የ10 ኪሎሜትር ውድድሩን በወንዶች ቢኒያም መሀሪ በሴቶች ደግሞ መልክናት ውዱ አሽንፈዋል። የውድድሩ አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የ200 ሺህ፣ 100 ሺህ እና 50 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።