ለወታደራዊ፣ ኮሙዩኒኬሽን እና ሌሎች ተግባራት የሚውሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶች ከምድር በላይ ይገኛሉ
ሳተላይት ወደ ህዋ በማምጠቅ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ቀዳሚዋ ሀገር ናት።
በፈረንጆቹ ጥቅምት 4 1957 ወደ ህዋ የመጠቀችው “ስፑትኒክ 1” ሳተላይት ትሰኛለች።
አሜሪካም ከአንድ አመት በኋላ በጥር ወር መጨረሻ 1958 “ኤክስፕሎረር 1” የተሰኘች ሳተላይት በማምጠቅ የህዋ ፉክክሩን ተቀላቅላለች።
የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት የአሁኗ ሩሲያ ሳተላይት በማምጠቅ ቀዳሚ ብትሆንም በርካታ ሳተላይቶችን በህዋ ላይ በማስፈር አሜሪካን የሚደርስባት አልተገኘም፤ ከ5 ሺህ በላይ ሳተላይቶች አሏት።
ወታደራዊ ሳተላይቶችን በማምጠቅም (123) አሜሪካ ቀዳሚዋ ናት።
ከሶቪየት ህብረት የተነጠሉ ሀገራት (1 ሺህ 546)፣ቻይና እና ብሪታንያም በርካታ ሳተላይት በህዋ ላይ ያላቸው ሀገራት ናቸው።
በህዋ ላይ በርካታ ሳተላይት ያላቸውን ሀገራት ይመልከቱ፦