የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጦራቸውን ወደ ሩሲያ እንዲመልሱ ተማፀኑ
ሩሲያ በዩክሬኗ ዶንባስ ክልል ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯን አስታወቀች
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይድን በዩክሬን ጉዳይ ዓለም ሩሲያን ተጠያቂ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸውን ወደ ሩሲያ እንዲመልሱ ተማጽኖዋቸውን አስምተዋል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬኗ ምስራቅ ዶንባስ ክልል ጦራቸውን በማስማራት ለዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማስጀመራቸው ትናት ምሽት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ይህን ተከትሎም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገራት መሪዎች ተማጽኖ እና ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክቶችን ለሩሲየ በመላክ ላይ ይገኛሉ።
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ፤ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸውን ከዩክሬን እንዲያስወጡ ተማጽነዋል
"ፕሬዝዳንት ፑቲን በሰብኣዊነት ስም ጦርህን ወደ ሩሲያ መልስ" ያሉት ጉቴሬዝ፤ ፐሬዚዳንቱ ይህንን ካላደረጉ ውጤቱ በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ጦርበነት ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው በሩሲያ ቤክሬን ላይ የምትፈጽመውን ወረራ ተከትሎ ለሚደርስ ጥፋት እና ውድመት ዓለም ሩሲያን ተጠያቂ ሊያድርግ ይገባል ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደበን አክለውም፤ “የዓለም ህዝብ በሩሲያ ጥቃት ጉዳት የሚደርስባቸው ዩከሬናውያንን በጸሎት ያስባል” ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የብሪታኒያወ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም “ሩሲያ ደም አፋሳሹን መንገድ ምርጣለች፤ ቀጣይ እርምጅ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ከዩክሬኑ ፐሬዚዳንት ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት ምሽት በቴልቪዥን በሰጡት መግለጫ፤ በዩክሬኗ ምስራቅ ዶንባስ ክልል ለዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማስጀመራቸውን ተናግረዋል።
የወታደራዊ ዘመቻው ዋነኛ ዓላማ “ላለፉት 8 ዓመታት በኬይቭ በሚገኘው መንግስት የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ሰዎችን ነፃ ማውጣት ነው” ሲሉ አስታውቀዋል።
ዩክሬን በበኩሏ፤ “ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሙሉ በሙሉ ወረራ መፈጸም ጀምረዋል” በማለት ከሳለች።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደምየትሮ ኩሌባ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ “በሰላማዊ የዩክሬን ከተማዎች ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ነው” ብለዋል።