የሩሲያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ከሩሲያ ውጪ እንዲሰማራ ፈቀደ
153ቱም የምክር ቤቱ አባላት ጦሩ ከሀገሪቱ ድንብር ውጪ እንዲሰማራ ውሳኔውን በሙሉ ድምጽ አጸድቀዋል
ምክር ቤቱ የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ላሉ ተገጣይ ግዛቶች ድጋፍ እንዲሰጥ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው
የሩሲያ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱ ጦር ከሩሲያ ድንበር ውጪ እንዲያሰማሩ የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉ ተነገሯል።
የሀገሪቱ ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን የሚገኙ ተገጣይ ግዛቶች እንዲደግፉ መሆኑን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያመለክታል።
የሩሲያ ጦር ከሀገሪቱ ውጪ እንዲሰማሩ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ ያለ ምንም ተቃውሞ እና ድምጸ ተአቅቦ በ153 የምክር ቤቱ አበላት ድጋፍ እንዳገኘ ታውቋል።
በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑተን ጠያቂነታ በተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ኒኮላይ ፓንኮቭ፤ “ከዩክሬን ጋር የሚደረግ ድርድር ቆሟል” ብለዋል።
“የዩክሬን ባለስልጣናት የግጭት እና ደም አፋሳሽ መንገድን መርጠዋል” ያሉት ኒኮላይ ፓንኮቭ፤ “ሌላ ምንም አማራጭ ሊሰጡን አልቻሉም” ሲሉም ተናግረዋል።
ወደ ዩክሬን ተገንጣይ ግዛቶች ድንበር ከፍተኛ የጦር ተሸከርካሪዎች እየተጠጉ መሆኑን ያነሱት ምክትል ሚኒስትሩ፤ ኔቶም ዩክሬንን ከፍተኛ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን ማስታጠቁን ገልጸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባሳለፍነው ሰኞ በምስራቅ ዩክሬን ለሚገኙ ተገንጣይ ክልሎች ለሆኑ ዶኔትስክ እና ሉጋንስክ እውቅና መስጠታቸው ይታወሳል።
የሩሲያ ጦር ወደ ሁለቱም ተገንጣይ የምስራቅ ዩክሬን ግዛች ውስጥ እንዲገባ የሚያስችል ስምምነትም በፕሬዝዳንት ፑቲን እና በአስገንጣይ ኃይሎች መካከል መፈረሙም ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ለተገንጣዮች እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ አለምአቀፍ ውግዘት አስከትሎባቸዋል፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በተገንጣዮቹ ግዛቶ ውስጥ የሚከናወነው የአሜሪካ የቢዝነስ እንቅስቃሴ እንዲቆም ትእዛት አስተላልፈዋል።
ፈረንሳይ እና ጀመርመንም ማእቀብ ለማጣል ተስማምተዋል፤ ብሪታኒያ እና አሜሪካም ተጨማሪ ማእቀብ እንደሚጥሉ አስታውቀዋል።
ቻይና በበኩሏ ሁሉም ወገኖች እንዲገደቡ የተየቀች ሲሆን፣ ጃፓን ሙሉ በሙሉ ወረራ በሚከሰትበት ጊዜ በሞስኮ ላይ የተጣለውን ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ለመቀላቀል ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።