አልዐይን ስለ አየር ንብረት ለውጥ መረጃ የሚሰጥ ስርዓት መዘርጋቱን ገለጸ
ኧርዝ ኮል የተሰኘው አዲሱ የመረጃ ስርዓት ለማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ ነው
ኮፕ28 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከአንድ ወር በኋላ በዱባይ ይካሄዳል
አልዐይን ስለ አየር ንብረት ለውጥ መረጃ የሚሰጥ ስርዓት መዘርጋቱን ገለጸ፡፡
በዓለም አቀፍ ዘገባዎቹ የሚታወቀው አልዐይን የዜና ተቋም ስለ ኮፕ28 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ መረጃ መስጠትን ዓለማው ያደረገ ስርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡
ኧርዝ ኮል የተሰኘው ይህ የመረጃ ቋት ሰዎች ስለ አየር ንብረት ለውጥ የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ሰዎች ስለ አየር ንብረት ለውጥ እና ዘላቂ ልማት ስራዎች ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ይህ የመረጃ ቋት በአረብ እና በመላው ዓለም ሀገራት ያሉ ሰዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ሰዎች ስለ አካባቢ ጥበቃ፣ ዘላቂ የሀይል አማራጮች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃዎችን እና ትንታኔዎችን ያቀርባል ተብሏል፡፡
ለዓለማችንን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለመስጠት 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ
እንዲሁም ለአየር ንብርት ለውጥ መፍትሄዎች፣ ፈተናዎች እና የባለሙያዎችን አስተያየት ያካተቱ ይዘቶች በትንታኔ መልኩ ተዘጋጅተው እንደሚቀርቡበትም ተገልጿል፡፡
የአልዐይን ዋና አዘጋጅ አህመድ አል አላዊ እንዳሉት “አዲሱ የመረጃ ስርዓት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ሁነቶች እና መረጃዎች የሚቀርቡበት ሲሆን ዜጎችን ስለ አየር ንብረት ለውጥ በቋሚነት ትክክለኛነታቸው በተረጋገጠ መልኩ የሚቀርቡበት ነው” ብለዋል፡፡
አልዐይን ሚዲያ ይህን የአየር ንብረት ለውጥ መረጃ ስርዓት የዘረጋው ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ሲል እንደሆነም ዋና አዘጋጁ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የመረጃ ስርዓት መሰረትም ትክክለኛነታቸው የተረጋገጡ ሳይንሳዊ ትንታኔዎች እና ለአየር ንብረት ለውጥ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የሚችሉ ይዘቶች እንደሚቀርቡበትም ዋና አዘጋጁ አህመድ አል አላዊ ገልጸዋል፡፡
የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወይም ኮፕ28 ከአንድ ወር በኋላ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ዱባይ ከተማ ይካሄዳል፡፡