የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች ምን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል?
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ጉዞን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል
የአንድ ሐጅ አድራጊ 315 ሺህ ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት ተገልጿል
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዘንድሮ የሐጅ ጉዞን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው ÷ የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መወሰኑን በመግለጫው ተመላክቷል።
ቀድሞ በፌደራል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ብቻ ይሰጥ የነበረው የምዝገባ አገልግሎት በዘንድሮው የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ወደ ሐጃጁ በማቅረብ ምዝገባውን በ16 ጣቢያዎች በየአካባቢው እንደሚከናወን ተገልጿል።
ለዚህ ቀደም የነበረውን የሐጃች ፍሰት መረጃን መሰረት በማድረግ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች ምዝገባ እንደሚከናወንም ምክር ቤቱ አስታውቋል።
የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች ምን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል?
ማንኛውም የሐጅ ተጓዥ ለአካ መቅረብ ይኖርበታል የተባለ ሲሆን፤ ለምዝገባ በሚጠቡት ጊዜም
የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ (መንጃ ፈቃድ)
የጉዞ ሰነድ (ፓስፖርት) የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ9 ወራ በላይ የቀረው
አንድ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
የኮቪድ 19 ክተባት የወሰዱበት ማስረጃ እንዲሁም የቢጫ ወባ የክትባ ካርድ ማቅረብ
ራሳቸቀውን ችለው የሐጅ ስርዓቱን የሚፈጽሙ ወይም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ክፍያ በመክፈል ደጋ ሰው ማቅረብ የሚችል
በሳዑዲ አረቢያ መንግስት ወደ ሳዑዲ እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸው ሰዎች እንዲሁም የሐጅን ጉዞ በመጠቀም ለሌላ ዓላማ የዘንድሪ የሐጅ ምዝገባ ማድረግ እንደማይቻልም ምክር ቤቴ አስታውቋል።