ልዩልዩ
ሳዑዲ ዘንድሮ የሐጅ ስርዓት ማከናወን የሚችሉት በሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችና ነዋሪዎች ብቻ መሆናቸውን ገለጸች
በድምሩ 60,000 ሐጆችን ብቻ እንደምታስተናግድም ሀገሪቱ ገልጻለች
ከየትኛውም የውጭ ሀገር ዘንድሮ የሐጅ ተጓዥ እንደማትቀበል ሳዑዲ አረቢያ አስታውቃለች
የሳዑዲ ሐጅና ኡምራ ሚኒስቴር የዘንድሮው 1442ኛ ሐጅ ለዜጎችና በሀገሪቱ ውስጥ ላሉት ነዋሪዎች ብቻ የሚወሰን መሆኑን አስታውቋል፡፡ በድምሩ 60,000 ሐጆችን ብቻ እንደሚያስተናግድም የገለጸው ሚኒስቴሩ ይህ ውሳኔ የተወሰነው በኮሮናቫይረስ ምክንያት መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
የሀጅ ስርዓቶችን ለመፈፀም በስፍራው የሚገኙ ሰዎች ስር የሰደደ በሽታ የሌለባቸው እንዲሁም የኮሮና ክትባትን የተከተቡ ፣ ከ 18 እስከ 65 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆን እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ግብፅ ለሳዑዲ አረቢያን ውሳኔ አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡