እስራኤል ከአንድ ወር በፊት በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት 32 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል
ጋዛን እያስተዳደረ ያለው ሀማስ ሀማስ ለእስራኤል መረጃ ስታቀብሉ ነበር ያለቸውን ሁለት ሰዎችን ጨምሮ አምስት ፍልስጤማዊያንን በስቅላት ቀጥቷል።
በሞት የተቀጡት ፍልስጤማዊያን በተለይም ሁለቱ በፈረንጆቹ 2015 እና 2009 ላይ ለእስራኤል ሰርታችኋል በሚል ቅጣቱ መተላለፉ በሀማስ ላይ ትችቶችን እያስከተለበት ይገኛል ተብሏል።
ፍልስጤማዊያን እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቋማት የሀማስን ድርጊት የኮነኑ ሲሆን መሰል ቅጣቶችን እንዲያቆምም ጠይቀዋል።
ሀማስ ከፈረንጆቹ 2007 ዓመት ጀምሮ በስቅላት የተቀጡ ፍልስጤማዊያን ቁጥር 27 የደረሰ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር መሀሙድ አባስ ላይ ትችቶች እየተሰነዘሩባቸው ይገኛል።
እስራኤል ከአንድ ወር በፊት በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት 32 ሰዎችን መግደሏ ይታወሳል።
የእስራኤል ጦር በዚህ ጊዜ ባደረሰው የሮኬት ጥቃቶች 32 ሰዎችን ከመግደሉ በተጨማሪ የእስላሚክ ጅሀድ ቡድን ዋና እና ምክትል መሪንም ገድለዋል፡፡
ከሟቾች በተጨማሪም ከ265 የሚልቁ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ገብተው የነበረ ሲሆን በወቅቱ የተኩስ አቁም መደረጉን ተከትሎ የተጎጂዎችን ቁጥር መቀነስ ተችሏል ተብሏል።
ከሟቾች ውስጥ ስድስቱ ህጻናት ፣አራቱ ደግሞ ሴቶች እንደሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የተኩስ አቁም ስምምነት ባይደረስ የሟቾች እና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችል እንደነበር ተጠቅሷል።