ፖለቲካ
ሀማስ ለእስራኤል ምላሽ ለመስጠት "በሙሉ አቅም" መዘጋጀቱን ተናገረ
ሀማስ ጦርነት ቆሞ በእጅ ያሉትን ታጋቾች ለመልቀቅ ቢስማማም እስራኤል ፍቃደኛ አልሆነችም
የውሳኔ ሀሳቡ እስራኤልና አሜሪካን ጨምሮ 14 ሀገራት ቢቃወሙትም፣ በአብላጫ ድሞጽ ጸድቋል
እስራኤል የመሬት ጥቃት ዘመቻ ማጠናከሯን ተከትሎ ሀማስ ምላሽ ለመስጠት በሙሉ አቅሙ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ጋዛን እያስተዳደረ ያለው ሀማስ እስራኤል በጋዛ የምትሰነዝረውን አጠናክራለች ከተባለ በኋላ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጦር ጋር መዋጋታቸውን ገልጿል።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤላ ሀጋሪ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከተደረገው ማጥቃት በተጨማሪ የእግረኛው ጦር ይዞታውን ያሰፋል ብለዋል።
ነገርግን ቃይ አቀባዩ እስራኤል ታደርገዋለች ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የእግረኛ ጦር ዘመቻ ስለመጀመሩ በግልጽ ያሉት ነገር የለም።
ቃል አቀባዩ በሀማስ በተቆፈሩ ቱቦዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረገው መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ሀማስ ጦርነት ቆሞ በእጅ ያሉትን ታጋቾች ለመልቀቅ ቢስማማም እስራኤል ፍቃደኛ አልሆነችም።
በትናንትናው እለት የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የአረብ ሀገራትን በወከለችው ጆርዳን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቃውማለች።
የውሳኔ ሀሳቡ እስራኤልና አሜሪካን ጨምሮ 14 ሀገራት ቢቃወሙትም፣ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
ነገርግን እስራኤል ተኩስ እንደማታቆም እና በውሳኔው እንደማትገዛ ገልጻለች።