የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ በጋዛ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል
የስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ሶስተኛ ሳምንቱን አስቆጥሯል።
ባለፈው ጥቅምት መጀመሪያ ሳምንት ሀማስ ድንበር በመጣስ ያደረሰውን ከባድ የተባለ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል መጠነ ሰፊ የአጸፋ ጥቃት በማድረስ ላይ ትገኛለች።
የእግረኛ ጦር ጥቃት
እስራኤል በዋናነት በአየር ድብደባ ስታደርገው የነበረውን ጥቃት በእግረኛ ወታደር ጀምራዋለች። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሀጋር በትናንትናው እለት ጦሩ በጋዛ ሰርጥ የመሬት ይዞታውን እያስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀማስ ይዞታ የሆነችው ጋዛ መብራት፣ ውሃ እና ምግብ እንዳታገኝ አድርጋ ከበባ ውስጥ በማስገባት ነው እስራኤል እያጠቃች ያለችው።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ
ተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የአረብ ሀገራትን በመወከል ጆርዳን የውሳኔ ሀሳብ አቅርባለች። የውሳኔ ሀሳቡ የሰብአዊ ተኩስ አቁም ይደረግ የሚል ሲሆን ጠቅላላ ጉባኤው በ120 የድጋፍ ድምጽ አጽድቆታል።
ይህን ውሳኔ አሜሪካ እና እስራኤልን ጨምሮ 14 ሀገራት ተቃውመውታል፤ ሌሎች 45 ሀገራት ደግሞ ድምጽ አልሰጡም።
ተመድ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢወስንም እስራኤል ማጥቃቷን ቀጥላበታለች
የሀማስ ምላሽ
ሀማስ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ገልጿል።
እስራኤልን ባጠቃበት ወቅት የያዛቸውን ሰዎች ለመልቀቅም የተኩስ አቁም ስምምነትን እንደቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።
ነገርግን እስራኤል ተኩስ ለማቆም ፍቃደኛ የማትሆን ከሆነ በሙሉ አቅሙ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።
የግጭቱ መስፋፋት እድል
ይህ ግጭት ወደ ጎረቤት ሀገራት ይስፋፋል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።እስራኤል ጥቃቱን ያደረሱት ለሀማሰ የወገኑ የሀውዚ ታጣቂዎች ናቸው፤ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ ብላለች።
በትናንትናው እለት የግብጿ ታባ ከተማ በሚሳይል መመታት ግጭቱ ይስፋፋል የሚለውን ስጋት ተጨባጭ ያደረገ ነው ተብሏል።