በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች
በእስራኤል እና በሀማስ መካከል ያለው ግጭት ምዕራባውያን እና የአረብ ሀገራት በሁለት የተለያዩ ጎራዎች አፋጧቸዋል
ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል
በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጿ ከተማ በሚሳይል ተመታች።
በእስራኤል ድንበር የምትገኘው የግብጽ የቀይ ባህር ከተማ ታባ በሚሳይል ተመታች።
እየተካሄደ ባለው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ምክንያት የተተኮሰው ሚሳይል ከጋዛ ሰርጥ 220 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የግብጿን የመዝናኛ ከተማ መምታቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሚሳይሉ በታባ የጤና ማዕከል ላይ ማረፉን እና ስድስት ሰዎችን ማቁሰሉን ዘገባው ጠቅሷል።
ታባ ግብጽን ከቀይ ባህሯ የእስራኤል ወደብ ኢላት የምታገናኝ ቦታ ነች።
የእስራኤል ጦር ከድንበር ውጭ ስለተፈጠረው የጸጥታ ችግር መረጃ እንዳለው ገልጿል።
ሀማስ በበኩሉ ባለፈው ሮብዕ እለት እንደገለጸው የእስራኤሏን ኢላት ኢላማ አድርጎ እንደነበር የገለጸ ቢሆንም የእስራኤል ጦር ከኢላት ወጣ ቦታ ማረፉን አስታውቋል።
የእስራኤል-ሀማስ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ባለፈው ጥቅምት ወዲህ ይህ የመጀመሪያው የረጅም ርቀት የፍልስጤም ጥቃት ነው ተብሏል።
የታባ ፍንዳታ የሚያሳየው ግጭቱ እየጠነከረ ሲሄድ ግብጹ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ተጎጂ እንደሚሆኑ ነው።
በእስራኤል እና ጋዛን በሚያስተዳድረው ሀማስ መካከል ያለው ግጭት ምዕራባውያን እና የአረብ ሀገራት በሁለት የተለያዩ ጎራዎች አፋጧቸዋል።
አሜሪካን ጨምሮ አብዛኞቹ ምዕራባውያን ሀገራት እስራኤል ራሷን እየተከላከለች ነው የሚል አቋም አላቸው፣ ተኩስ አቁም እንዲደረግም አይፈልጉም።
የአረብ ሀገራት በአንጻሩ ግጭቱ እንዲቆምና ሰላማዊ መፍትሄ እንዲመጣ ይፈልጋሉ።
ያለማቋረጥ የአየር ጥቃት እያደረሰች ያለችው እስራኤል ጋዛን በመክበብ የእግረኛ ወታደር ወረራ ለማድረግ ተዘጋጅታለች።