አልቃሳም ብርጌድ "የወራሪ ሀይሎች ጭፍጨፋ እና የግድያ ፖሊሲ" እስከቀጠለ ድረስ "በእስራኤል ውስጥ የሰማዕትነት ዘመቻ" ይቀጥላል ብለዋል
ሀማስ በእስራኤል ለደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደ።
የሀማስ ታጣቂ ክንፍና እስላማዊ ጅሀድ የእስራኤል ፖሊስ እና የሀገር ውስጥ ደህንነት የሽብር ጥቃት ነው ሲሉ ለገለጹት በቴላቪቭ በሚገኝ ምኩራብ አቅራቢያ ለደረሰው ፍንዳታ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ በዛሬው እለት አስታውቀዋል።
ምኩራብ አካባቢ የፈነዳውን ቦምብ የተሸከመው ግለሰብ መገደሉን እና አንድ መንገደኛ ደግሞ መቁሰሉን ፖሊስ ገልጿል።
የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ አልቃሳም ብርጌድ ባወጣው መግለጫ "የወራሪ ሀይሎች ጭፍጨፋ እና የግድያ ፖሊሲ" እስከቀጠለ ድረስ "በእስራኤል ውስጥ የሰማዕትነት ዘመቻ" ይቀጥላል ብለዋል።
ይህ ፍንዳታ የተከሰተው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 10 ወራትን ያስቆጠረው የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት በተኩስ አቁም እንዲቋጭ ጥረት ለማድረግ ቴልአቪቭ ከደረሱ ከአንድ ሰአት በኋላ ነው።
በቀጣናው ያለው አሁናዊ ውጥረት የተኩስ አቁሙን መደረስ አስፈላጊነት አንገብጋቢ አድርጎታል።
የሀማስ የፖለቲካ መሪ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው እስማኤል ሀኒየህ በቴህራን፣ የሄዝቦላ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሹክር በቤሩት ከተማ ዳርቻ መገደል በመካከለኛው ምስራቅ የነበረው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጎታል።
ኢራን እና አጋሮቿ ሀማስ እና ሄዝቦላ ለግድያዎቹ እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል፤ እንደሚበቀሏትም ዝተዋል።
የሄዝባለ ወታደራዊ አዛዥ ግድያ ኃላፊነት የውደችው እስራኤል፣ በሀኒየህ ግድያ ዙሪያ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠችም።
ኢራን የበቀል እርምጃዋን ልትተው የምትችለው፣ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ብቻ መሆኑን ገልጻልች።
የተኩስ አቁም ንግግሩ ችላ መባል የለበትም የምትለው አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ብሊንከንን ወደ እስራኤል ልካልች።