እስራኤል በፍልስጤማዊ እስረኛ ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ወሲባዊ ጥቃት እየመረመርኩ ነው አለች
ተመድ በእስራኤል ወታደሮች በፍልስጤማዊው እስረኛ ላይ ደርሷል የተባለውን "ዘግናኝ ግፍ" ሲል አውግዘዋል
የሀማስ ፖለቲካዊ መሪ ሀኒየህ መገደል በመካከለኛው ምስራቅ የበረው ውጥረት እንዲያይል አድርጎታል
እስራኤል በፍልስጤማዊ እስረኛ ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ወሲባዊ ጥቃት እየመረመርኩ ነው አለች።
እስራኤል በፍልስጤማዊ እስረኛ ላይ ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ ጥንካራ ምርመራ እንደምታደርግ እና እስረኛ አያያዝን በተመለከተ ለአለማቀፍ ህግ ተገዥ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት ገልጿል።
የተመድ ሰፔሻል ራፖርተር ኦን ቶርቸር በእስራኤል ወታደሮች በፍልስጤማዊው እስረኛ ላይ ደርሷል የተባለውን "ዘግናኝ ግፍ"ሲሉ አውግዘዋል።
የእስራኤል ጦር፣ አቃቤ ህጎች በፍልስጤማዊው እስረኛ ላይ ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ወታደሮች በቁም እስር ላይ እንዲቆዩ መጠየቃቸውን እና እስራቸው እስከሚቀጥለው ማክሰኞ መራዙም ባለፈው ማክሰኞ እለት አስታውቆ ነበር።
የእስራኤል ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከሆነ ወታደሮቹ የሀማስ ልዩ ተዋጊ አባሉን በደቡባዊ እስራኤል ኔጌቭ በረሃ ውስጥ በሚገኘው ስዴ ቴይማን እስር ቤት አድርሰውበታል ተብለው መከሰሳቸውን ዘግበዋል።
"እስራኤል ለህግ የበላይነት መከበር እና ለእስረኞች ሰብአዊ አያያዝ ቁርጠኛ መሆኗን እና ማናቸውም ተፈጽመዋል የሚባሉ ጥቃቶች በእስራኤል ባለስልጣናት ሳይንሳዊ ጥናት ይካሄድባቸዋል" ብሏል ሚኒስቴሩ።
ተመድ፣ ሀማስ ባለፈው ጥቅምት የእስራኤል ድንበር በመጣስ በፈጸመው ጥቃት 1200 ሰዎችን ከገደለ እና ከ250 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አግቶ ከወሰደ ጀምሮ በፍልስጤማውያን እስረኞች ላይ ግፍ ይፈጸምባቸዋል የሚሉ በርካታ ሪፖርቶች እየደረሱት እንደሆነ እየገለጸ ነው።
ለረጅም ጊዜ ሀማስ የፖለቲካ መሪ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው እስማኤል ሀኒየህ በቴህራን፣ የሄዝቦላ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሹክር በቤሩት ከተማ ዳርቻ መገደል በመካከለኛው ምስራቅ የነበረው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጎታል።
ኢራን እና አጋሮቾ ሀማስ እና ሄዝቦላ ለግድያዎቹ እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል፤ እንደሚበቀሏትም ዝተዋል።
ኢራን የበቀል እርምጃዋን ልትተው የምትችለው፣ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ብቻ መሆኑን ገልጻልች።
የተኩስ አቁም ንግግሩ ችላ መባል የለበትም የምትለው አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ብሊንከንን ወደ እስራኤል ልካልች።