“ሃምስተር ኮምባት” ምንድን ነው?: ህጋዊ ወይስ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው?
“ሃምስተር ኮምባት” በቅርብ ጊዜ በቴሌግራም ላይ የተመሰረተ የክሪፕቶ ጨዋታ ነው
ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ “ሃምስተር ኮምባት” በበርካቶች እየተዘወተረ መጥቷል
“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች ዘንድ እየተዘወተረ የመጣ በቴሌግም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ተጫዋቾቹ በየቀኑ ስክሪናቸውን በጣታቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ሲያደርጉ ክሪፕቶ ሳንቲሞችን የሚያገኙበት ነው።
“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ በበርካቶች እየተዘወተረ የመጣ ጨዋታም ሆኗል።
በቴሌግራም ላይ የተመሰረተው ሃምስተር ኮምባት በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ተጫዋቾችን በማፍራት ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።
ሃምስተር ኮምባት ምንድን ነው?
ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው።
እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።
ምናልባት ጨዋታ ብቻ ስለሆነ ዋናው ጥቅሙ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሊያስከትል ይችላል፤ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ጨዋታ ቢሆንም፣ በሃመስተር ኮምባት የሰበሰብናቸው ሳንቲች (ኮይኖች) ኤርድሮፕ የመሆን ዝግጅት እንዳለ ነው የሚነገረው።
ይህ ማለትም በዚህ ጨዋታ ሳንቲሞችን (ኮይን) የሰበሰቡ ተጫዋቾች በቲ.ጂ.ኢ (ቶከን ጄኔሬሽን ኢቨንት) ወቅት ለኤር ድሮፕ ብቁ የመሆን እንደል አላቸው።
ሳንቲሞቹ አስተዳዳሪዎች ያዋጣል ብለው ያመኑትን ማንኛውንም ተመን በመጠቀም ወደ ቶከን ይቀየራሉ፤ ስለዚህ “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) መጫወት ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ነው የተባለው።
ሃምስተር ኮምባት ህጋዊ ወይስ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው?
“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) በክሪፕቶ ገንዘብ ተፈጥሮ ምክንያት ህጋዊ ወይም ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ምንም መንገድ የለም።
ነገር ግን ሃምስተር ኮምባት ጠቃሚ ነገር ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም አንዱ ማሳያዎ እንደ “BingX” ካሉ ልውውጦች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩ ነው።
ይህ ማለት ወደፊት በ”BingX” ልውውጥ ላይ የሃምተርን ተመዝግቦ ልናይ እንችላል፤ ነገርግን አሁን ማድረግ ያለብን ማመን እና ጨዋታውን መጫወት ብቻ ነው።
ተለዋዋጭ በሆነው እና ተገማች ባልሆነው በክሪፕቶ ዓለም ውስጥ ማድረግ የምንችለው እንድ ነገር ወይ አምኖ መጫወት አሊያም መተው ብቻ ነው።
ሃምስተር ኮምባት እንዴት መጀመር እንችላለን?
መጀመሪያ የሃምስተር ኮምባት ቦት ማስጀመር ያስፈልጋል፤ ይህን ለማድረግም የቴሌግም አካውንት እና ሊንክ የሚያስፈልገን ሲሆን፤ አካውንት ለመክፈት ወደ ፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ጎራ በማለት ቴሌግራምን ስልካችን ላይ በመጫን መክፈት እንችላለን።
የቴሌግራም አካውንት ከከፈትን በኋላ የቴሌግራም መፈሊጊያ (search button) ላይ ‘Hamster Kombat’ የሚለውን በማስገባት በምንፈልግበት ወቅት የሃምስተር ኮምባት ቦት የሚመጣልን ሲሆን፤ እዚያ ውስጥ ስንገባ እንኳ ደህና መጣችሁ የሚለውን ተከትሎ የተለያዩ ጀምር (start) የሚል እና ሌሎች አማራጮች ይመጡልናል።
ጀምር (start) የሚለውን አማራጭ ስንከፍትም ወደ ዋናው የጨዋታው ግጽ የሚወስደን ይሆናል።
“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ተጫዋቾች ያለመታከት በተከታታይ የስልካቸውን ስክሪን በጣጣቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ባደረጉ ቁጥር እስከ 2000 እና ከዚያ በላይ ኮይን ያገኛሉ።
ከታፕ የምናገኘውን የሳንቲም ቁጥር ለመጨመር ወደ ቡስት ገጹ በመግባት አስፈላጊ የሆኑ ሂደቶችን በመከተል ማሳደግየምንችል ሲሆን፤ ይ ግን የተወሰኑ ሳንቲችን (ኮይን) ሊያስወጣን ይችላል።