ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካዊት ሴት ፕሬዝዳንት ተሾመለት
ክላውዲን ጌይ ታዋቂውን ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በፕሬዚዳንትነት በመምራት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት ሆነዋል
አዲሷ ፕሬዝዳንት ይህን ኃላፊነት በመያዝ ደግሞ ሁለተኛዋ ሴት ናቸው።
ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካዊት ሴት ፕሬዝዳንት ተሾመለት
በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የኪነጥበብ እና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የነበሩት ክላውዲን ጌይ፤ ሎውረንስ ባኮንን በመተካት የዝነኛው ዩኒቨርስቲ 30ኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
ይህም የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት እና ሁለተኛዋ ሴት አድርጓቸዋል።ኃላፊነታቸውንም በሚቀጥለው ዓመት ሀምሌ ወር ላይ እንደሚጀምሩ ተነግራል።
የ52 ዓመት እድሜ ያላቸው አዲሷ ፕሬዝዳንት በካምብሪጅ ማሳቹሴትስ የሚገኘው ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ቅበላ ፖሊሲው ላይ ፈተናዎች በገጠሙት በዚህ ጊዜ ኃላፊነታቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሃርቫርድ የአሜሪካን ህገ-መንግስት እንደሚጥስ እና የአመልካቾችን ዘር ግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪዎችን እንደሚያገል የሚገልጽ የ2014 ክስ ለማየት ተስማምቷልም ነው የተባለው።
ጌይ በመግለጫው ላይ "ከጀርባችን ባለው የዚህ ያልተለመደ ተቋም ጥንካሬ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ጥልቅ ትብብርን በሚጠይቅበት ጊዜ ላይ ነን" ብለዋል።
"ሃርቫርድ ከዓለም ታላቅ ፈተናዎቻችን ፈር ቀዳጅ አስተሳሰቦችን ለማምጣት አስቸኳይ ስራ አለበት" ሲሉም ትኩረታቸውን ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው በፈረንጆቹ 1936 ላይ የተመሰረተ አንጋፋ ተቋም ሲሆን በ2022 የ50 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ልገሳ ተደርጎለታል ተብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ አንጋፋው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሲሆን፤ ባራክ ኦባማን ጨምሮ ስምንት የሀገሪቱን ፕሬዚዳንቶችን አስተምሯል።