ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ከ1ኛ እስከ 8ኛ ተከታትለው በመግበት አሸነፉ
የዩጂን ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
በሴቶች 1500 ሜትር ድርቤ ወልተጂ ስታሸንፍ፤ ጉዳፍ ፀጋይ በ10 ሺህ ሜትር 2ኛ ወጥታለች
በሄይዋርድ ፊልድ በተካሄደው የዩጂን ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
ትናንት ሌሊት በተካሄደው ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶ በተለያየ ርቀት ተከታትለው በመግባ ድል ማስመዝገባቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተለይም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ከ1ኛ እስከ 8ኛ ተከታትለው በመግበት ማሸነፋቸው ተነግሯል።
በዚህም መሰረት
በ5000 ሜትር ሴቶች
1ኛ ፅጌ ገብረሰላማ 14:18.76 (WL)
2ኛ እጅጋየሁ ታዬ 14:.18.92
3ኛ ፋሬወይኒ ሃይሉ 14:20.61
4ኛ አይናዲስ መብራቱ 14:22.76
5ኛ ብርቄ ሃየሎም 14:23.71 (WU20R)
6ኛ ሂሩት መሸሻ 14:33.44
8ኛ ሰናይት ጌታቸው 14:35.27 በመሆን ተከታለው በመግባት አሸንፈዋል።
በ1500 ሜትር ሴቶች ውድድርም ኢትዮጵያውቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ 3:53.75 በሆነ ሰዓት በመግባ ውድድሩን 1ኛ ደረጃ በመያዝ ስታጠናቅቅ፤ አትሌት ሀብታም አለሙ 4:00.44 በሆነ ሰዓት 10ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 29.05.92 በሆነ ሰዓት በመግባ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋንም ነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ የሚያመለክተው።
በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቺቤት 28:54.14 በሆነ ሰዓት በመግባት የርቀቱን ክብረወሰን በእጇ አስገብታለች።
ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቺቤት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድርን ከ29 ደቂቃ በታቸች የጨረሰች የዓለማችነ የመጀመሪያዋ አትሌት መሆንም ችላለች።