አትሌት ለተሰንበት ግደይ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች
ለተሰንበት ግደይ “2023 የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ” ብላለች
“ሲፋን ስትወድቅ ልቤ ተሰበረ፤ የውድቀትን ስሜት አውቃለሁ" ብላለች አትሌት ለተሰንበት
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች፡፡
የአምስት እና 10 ሺህ ሜትር ስኬታማ አትሌት ለተሰንበት በዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ ያሳየችው ድርጊት ለሽልማት አብቅቷታል፡፡
አትሌቷ በዚህ ድርጊቷ የዓመቱ ጨዋ የስፖርት ሰው በሚል በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሽልማት ተበርክቶላታል፡፡
ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማበረታታት ከስፖርታዊ ውድድር በተጓዳኝ ለየት ያሉ አወንታዊ ተግባራትን የሸለሙ አትሌቶችን ይሸልማል፡፡
በዘንድሮው ውድድርም በሀንጋሪ መዲና ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ውድድሩ መጨረሻ ላይ መውደቋን ተከትሎ እና አትሌቷ ከወደቀችበት እንድትነሳ ያደረገችላት ድጋፍ ለአሸናፊነት አብቅቷታል፡፡
አትሌት ለተሰንበትም በተደረገላት ሽልማት ደስተኛ መሆኗን ተናግራ “አትሌት ሲፈን ስትወድቅ በጣም አዝኜ ነበር፣ የመውደቅን ስሜት አውቀዋለሁ” ብላለች፡፡
ከነሀሴ 13 ቀን እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ሲካድየ ቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 195 የዓለማችን ሀገራት መሳተፋቸው ይታወሳል፡፡
አትሌት ትግስት አሰፋ በዓለም ምርጥ የዓመቱ አትሌቶች ዝርዝር ለመጨረሻው ዙር አለፈች
ከማጣሪያ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ 2 ሺህ 100 አትሌቶች በተሳፉበት በዚህ ውድድር ላይ 50 አትሌቶች የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ሲያስገኙ 48 የብር እንዲሁም 50 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ተወዳዳሪዎቹ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡
ውድድሩን 400 ሺህ ተመልካቾች በአካል ስታዲየም ገብተው ታድመውታል የባለ ሲሆን ሀንጋሪ ደማቅ እና አይረሴ ውድድር ማዘጋጀቷ ተገልጿል።
በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው ይህ ውድድር 52 አይነቶች የተካሄደ ሲሆን አሜሪካ በበላይነት አጠናቃለች።