አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ አንደኛ መውጣት እየቻለች በስህተት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመሄዷ 1ኛ ደረጃን አጥታለች
በአትላንታ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የአትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በስህተት 10 ሺህ ዶላር አጣች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ አትላንታ በተካሄደው የ10 ሺህ ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ ሁለተኛ ወጥታለች።
አትሌቷ ውድድሩን በአንደኝነት እየመራች እያለች ከፊቷ የነበረውን የውድደሩ መጨረሻ ላይ መንገድ ሲመራ የነበረው ሞተረኛ መንገድ ለመልቀቅ ሲወጣ መከተሏ ለስህተት ዳርጓታል ሲል ሲኤን ኤን ዘግቧል።
- ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶን ውድድሩን ያካሄደው አትሌት አበጀ አያና የፓሪስ ማራቶን አሸናፊ ሆነ
- የ17 ዓመቱ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ የካርልስሩሄ ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር 3000 ሜትር አሸናፊ ሆነ
በዚህም ውድድሩን ለማሸነፍ ተቃርባ የነበረችው ኢትዮጵያውቷ አትሌት ሰንበሬ የአንደኝነት ደረጃዋን ለሌላኛዋ አትዮጵያዊት አትሌት አሳልፋ ለመስጠት ተገዳለች።
በሰንበሬ ስህተት ምክንያም አትሌት ፎቴይን ተስፋይ ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችላለች። አትሌት ፎቴይን ተስፋይ ውድድሩን 30 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ በመግባት ያጠናቀቀች ሲሆን፤ መንገድ ስታ የነበረችው አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ወደ ውድድሩ በመመለስ ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች።
የዚህ ውድድር አሸናፊ 10 ሺህ ዶላር ወይም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ሽልማት የተሸለመ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ 5ሺህ ዶላር ተሸልሟል።
ሰንበሬ ቱፈሪ ውድድሩን ከኋላ ተነስታ ሶስተኛ ሆና ያጠናቀቀች ሲሆን የሶስት ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝታለች።