በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን ከ1 እስከ 5 ተከታትለው መግባት ችለዋል
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እና አትሌት ለሜቻ ግርማ በቻይና ዢያሜን በተካሄደ የ2024 ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ውድድርን በአሸናፊነት አጠናቀቁ።
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በቻይና ዢያሜን በተካሄደ ዳይመንድ ሊግ ውድድርን በ1500 ሜትር አሸንፋለች።
የ5000 ሜትር ሪከርድ ባለቤት የሆነችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ዛሬ በዢያሜን ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ በ1500ሜትር በታሪክ 3ኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች።
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50.30 በመሆን በመግባ ነው ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው።
በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን ከ1 እስከ 5 ተከታትለው መግባት የቻሉ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በመከተል፤ አትሌት ብርቄ ኃሎም 2ኛ፣ አትሌት መርቅነሽ መሰለ 3ኛ፣ አትሌት ድሪቤ ወልተጂ 4ኛ እንዲሁም አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃዋል።
በተያያዘ ዜና በወንዶች የ2024 የዲያመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በ5000 ሜትር የሩጫ ውድድር አሸንፏል።
አትሌት ለሜቻ ግርማ ርቀቱን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 12:58.96 ስዓት ፈጅቶበታል።
የ2024 ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ6 ወራት የሚቆይ ሲሆን፤ በአራት አህጉራት በ15 ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።