በሙቀት ሳቢያ ባለፉት 3 ወራት ከ24 ሺህ በላይ ሰዎች በስትሮክ ተጠቅተዋል
በህንድ ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በሀገሪቱ ያጋጠመውን ከፍተኛ ሙቀት ተከትሎ 33 ገደማ ሰዎች በሰሜናዊዋ ኡታህ ፓርዴሽ ክልል ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በኦዲሻ ደግሞ 20 ገደማ ሰዎች በሙቀት ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።
በህንድ በየዓመቱ በከፍተኛ ሙቀተ ከሚጠቁ ሀገራት መካከል ስትሆን፤ የዘንድሮው ግን ከዚህ ቀደም ከነበሩት ክብረወሰን የሰበረ ነው ተብሏል።
የህንድ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባጋመተው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ከ56 በላይ ሰዎች በስትሮክ ተጠቅተው ህይወታቸው አልፏል።
ባለፉት ሶስት ወራ ማለትም ከመጋት እስከ ግንቦት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 24 ሺህ 849 በለይ ህንዳውያን በስትሮክ ሀመም መጠቃታቸውን ነው የጤና ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
የህንድ ጤና ሚኒስቴር ይህንን ቢልም በሙቀት ሳቢያ በስትሮክ የተጠቁ እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር ከዚህም ሊልቅ እንደሚችል ተነግሯል።
በሙቀቱ ሳቢያ በርካታ የምርጫ አስፈጻሚዎችም ህይወት አልፏል የተባለ ሲሆን፤ በተለይም በኡታህ ፓርዴሽ ፖሊስ፣ የምርጫ ጣቢያ ኃላፊ እና የምርጫ ጣቢያ ሰራተኞች በስራ ላይ እያሉ ከሞቱት መካከል ናቸው።
በከባድ ሙቀት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ በአሜሪካ እና ህንድ ከባድ ሙቀት ከሚጠቁ ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።
ባለፈው አመት ከ62 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ከባድ ሙቀትና ወበቅ በዚህ አመትም ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው ተብሏል።