የፊሊፊንስ ትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በአካል እንዳይገኙ የትምህርት መርሃግብር ለሁለት ቀናት ሰርዟል
በደቡብ እስያ ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ የሙቀት ምክንያት ተዘግተዋል።
ፊሊፊንስ ትምህር ቤቶችን ስትዘጋና በኃይል መሰረተ ልማቷ ላይ ጫና እንደሚፈጠር ስታስጠነቀቅ በመላው የደቡብ እሲያ ደግሞ ባለስልጣናት በተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት ሞገድ የጤና ችግር ሊከሰት ይችላል በሚል የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል።
የፊሊፊንስ ትምህርት ሚኒስቴር በትናንትናው እለት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በአካል እንዳይገኙ የትምህርት መርሃግብር ለሁለት ቀናት ሰርዟል።
"ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ድብርት እና ራሳቸውን ስተው የወደቁ ተማሪዎች መኖራቸውን የሚያሳዩ ሪፖርቶች ደርሰውናል"ሲል የቲቸርስ ዲግኒቲ አሶሴሽን ሊቀመንበር የሆኑት ቤንጆ ባሳስ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
የተጨናነቁ እና ማናፈሻ የሌላቸው ትምህርት ቤቶች ባሉባት ፊላፊንስ በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት አማካኝ የሙቀት መጠን እስከ 37 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሚደረስ ተተንብይዋል።
የሀገሪቱ የአየርንብረት ኤጀንሲው የሰውነት ሙቀት መጠን 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሚደርስ እና ይህም ለስትሮክ ስለሚያጋልጥ ትምህርት ቤቶችን "አደገኛ" ቦታ ያደርጋቸዋል ብሏል።
የሙቀት መጠን መጨመሩ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ 1/3 ድርሻ ለምታበረክተው ለዋነኛዋ ሉዞን ደሴት በሚደርሰው የኃይል አቅርቦት ላይ ጫና እንደሚያሳድር የፊሊፊንስ ግሪድ ኦገሬተር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ እና በሀገሪቱ ማዕከላዊ እና ሰሜናዊ ክፍልም የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እደሚበልጥ ሲገመት የሀገሪቱ የሜትሮሎጂካል ኤጀንሲ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ከቤት ወጥተው እንዳይቆዩ መክሯል።
ባለፈው ሚያዝያ 22 በሰሜናዊቷ ላምፓንግ ከተማ 44.2 ዲግሪሴንቲግሬድ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል። ይህ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በዚህ ሳምንትም ሊቀጥል እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።
የታይላንድ የጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ወር በከፍተኛ ሙቀት አማካኝነት በተፈጠረ ስትሮክ 30 ሰዎች ሞተዋል።
በተመሳሳይ በቬትናም ከፍተኛ ሙቀት በመከሰቱ ሰዎች ኤየርኮንዲሽን ወይም የአየር ማናፈሻ ባለባቸው የገበያ አዳራሾች ራሳቸውን ሲያቀዘቅዙ ታይተዋል።
የሀገሪቱ ናሽናል ዌዘር አጀንሲ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ40.2-44.0 ዲግሪሴንቲግሬድ ሙቀት መመዝገቡን እና ይህም እስከ ረቡዕ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ማሌዥያ፣ ሲንጋፖር እና ኢንዶኔዥያ የሙቀት ሞገድ አጋጥሟቸዋል።