በተለይም በምዕራባዊ የሃገሪቱ አካባቢዎች የከፋ ነው የተባለለት ሙቀቱ የብዙዎችን ህይወት አደጋ ላይ እንዳይጥልም ተሰግቷል
በካናዳ ካጋጠመው ከፍተኛ ሙቀት ጋር በተያያዘ በርካቶች እየሞቱ ነው ተባለ፡፡
ከፍተኛ ሙቀቱ በቫንኩቨር፣አልበርታ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያጋጠመ ነው፡፡
ካሳለፍነው አርብ ጀምሮ 134 ሰዎች ሞተዋል ያለው የአካባቢው ፖሊስ ሞቱ ካጋጠመው ከፍተኛ ሙቀት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል፡፡
ከሙቀቱ ጋር የተያያዙ ናቸው ያላቸው 65 ድንገተኛ ሞቶች ሪፖርት እንደደረሰውም ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ካናዳ ከመቼውም ጊዜ የከፋ ነው የተባለ ከፍተኛ ሙቀትን እያስተናገደች ነው፡፡
ባለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የ49.5 ዲግሪ ሴልሺስ ልኬት ያለው ሙቀት መመዝገቡንም ነው የሃገሪቱ ሜትዮሮሎጂ አገልግሎት ያስታወቀው፡፡
ይህ በተለይም በምዕራባዊ የሃገሪቱ አካባቢዎች የከፋ ነው የተባለለት ይህ ሁኔታ የብዙዎችን ህይወት አደጋ ላይ እንዳይጥልም ተሰግቷል፡፡
በተለይ በእድሜ ለገፉና ተጓዳኝ የጤና እክሎች ላሉባቸው ትልቅ ስጋትን የደቀነም ነው፤ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል እንዳሉት እንደ ሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘገባ፡፡
ለመተንፈስ የሚያዳግ ከፍተኛ ወበቅን ያስከተለው ከፍተኛ ሙቀት በተለያዩ ሰሜን ምዕራባዊ የአሜሪካ ግዛቶች ማጋጠሙም ነው የተነገረው፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ለዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት መሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል፡፡
ሞቃታማው ዓመት ሆኖ ከተመዘገበው የጎርጎሮሳውያኑ 2019 ወዲህ ያሉት ተከታታ ዓመታት ሙቀት ከፍ ያለ ስለመሆኑም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡