ክልያን ምባፔ ከሞሮኳዊት እናቱ እና ካሜሩናዊ አባቱ ቢወለድም ላሳደገችው ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እየተጫወተ ይገኛል
ክሊያን ምባፔ የትውልድ ሀገሩን እየጎበኘ ነው።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል እና የፒኤስጂ እግር ኳስ ክለብ አጥቂ የሆነው ክሊያን ምባፔ የትውልድ ሀገሩ የሆነችው ካሜሩንን እየጎበኘ ነው።
ከ24 ዓመት በፊት በፈረንሳይ ፓሪስ የተወለደው ምባፔ በአባቱ ካሜሩናዊ ሲሆን የእናቱ የዘር ግንድ ደግሞ ከሞሮሎ ይመዘዛል።
ተጫዋቹ ከአባቱ ዊልፍሬድ ምባፔ ጋር በመሆን ለሶስት ቀናት ያህል የዘንድሮውን የክረምት ጊዜ ለመጎብኘት ወደ ትውልድ ሀገሩ አምርቷል።
ክሊያን ምባፔ የአባቱን ሀገር ካሜሩንን ሲጎበኝ ይህ የመጀመሪያ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።
የክሊያን ምባፔ የካሜሩን ጉብኝት በሀገሪቱ ትልቁ መነጋገሪያ ጉዳይ የሆነ ሲሆን በሉዋንዳ እና ያውንዴ ያሉ የሀገሪቱ ታሪካዊ ስፍራዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እና የፒኤስጂ እግር ኳስ ክለብ አጥቂ የሆነው ምባፔ ሪያል ማድሪድን ሊቀላቀል እንደሚችል እየተገለጸ ይገኛል።
በፒኤስጂ ክለብ የአንድ ዓመት ኮንትራት ብቻ የቀረው ምባፔ በክለቡ አዲስ ኮንትራት የመፈረም ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል ተብሏል።
ፒኤስጂ ምባፔን በሚቀጥለው ዓመት በነጻ ዝውውር ከሚለቀው ይልቅ ከወዲሁ ለሌላ ክለብ ሊሸጡት እንደሚችል አስታውቋል።
ከሪያል ማድሪድ በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናልም የክሊያን ምባፔ ፈላጊዎች ሆነዋል።
የምባፔ ቀጣይ ማረፊያ ክለብ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚሆን ወኪሉ ለስካይ ስፖርት ከሰሞኑ ተናግሯል።