"አይኤስን ለማሸነፍ ቁርጠኛ መሆናችንን አሳይተናል" ሲል የአሜራካ ማዕከላዊ ኮማንድ አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ኩሪላ ተናግረዋል
የአይኤስ መሪ በሶሪያ ምስራቃዊ ክፍል መገደሉን አሜራካ አስታወች።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው የአይኤስ መሪ በምስራቅ ሶሪያ በአየር ጥቃት ተገድሏል።
ማዕከላዊ ኮማንዱ እንደገለጸው ኡሳማህ አል-ሙሀጅር የተገደለው ባለፈው አርብ እለት ነው።
"አይኤስን ለማሸነፍ ቁርጠኛ መሆናችንን አሳይተናል" ሲል የአሜራካ ማዕከላዊ ኮማንድ አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ኩሪላ ተናግረዋል።
ጄነራሉ አይኤስ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን ከቀጣናው ባሻገር የደህንነት ስጋት ነው ብለዋል።
አይኤስ እና በኢራቅ እና በሶሪያ ያሉትን አጋሮቹን ለማጥፋት የሚደረገው ዘመቻ የሚያበቃው ቡድኑ ሲሸነፍ ነው ያለው ማዕከላዊ ኮማንዱ አርብ እለት በተደረገው ጥቃት ንጹሃን አልተገደሉም ብለዋል።
አርብ እለት በአይኤስ ላይ የተደረገው ጥቃት በድሮን የተፈጸመ ነው ተብሏል።
በፈረንጆቹ 2014 አይኤስ 1/3 የሚሆነውን የኢራቅ እና ሶሪያ ግዛት ይዞ የነበረ በመሆንም በሁለቱም ሀገራት ተሸንፏል።