በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን የጣለው ከባድ ዝናብ የሰው ሕይወት አጠፋ
በአሁኑ ጊዜ ተጎጂዎችን ለመታደግ የሚያስችሉ የነፍስ አድን ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ነው የአካባቢው የአስተዳደር አካላት የገለጹት
ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ባደረሰው በዚህ ዝናብ ምክንያት 156 የቤተሰብ አባላት ተፈናቅለዋል ተብሏል
በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ወረዳ ከባድ ዝናብ ጥሎ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን በድቡብ ክልል የጌዴኦ ዞን አስታወቀ፡፡
በዞኑ ይርጋ ጨፌ ወረዳ በጣለው ከባድ ዝናብ በወረዳው የጭቶ፣ ዶማርሶና ቡዱቅሳ ቀበሌዎች ላይ አደጋ ተከስቷል፡፡
በአዲስ አበባ ባጋጠመው የጎርፍ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ
የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ታደሰ ለጌዴኦ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ እንዳሉት በጣለው ከባድ ዝናብ አንድ ግለሰብ ሕይወቱ ሲያልፍ የ39 አባወራዎች 156 የቤተሰብ አባላት ተፈናቅለዋል፡፡
ጉዳት ከደረሰባቸው ቀበሌዎች አንዱ የሆነው የዶማርሶ ቀበሌ ነዋሪ እና የአይን እማኝ፤ አደጋዉ መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ድረስ በጣለዉ ከባድ ዝናብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ በሰሜን ሸዋ የአንድ ቤተሰብ አባላትን ህይወት ቀጠፈ
ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉት አባወራዎች በቤተሰቦቻቸውና በጎረቤቶቻቸው ቤቶች መጠለላቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው በአሁኑ ጊዜ የነፍስ አድን ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አደጋው በደረሰባቸው አከባቢዎች ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስተዳዳሪዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡