ህጻኑ በየመኗ አል-በይዳ ግዛት በሆነው የራዳአ ከተማ ነው የተወለደው
አለማችን ብዙ ለማመን የሚከብዱ አስደናቂ ነገሮችን እያስተናገደች ሲሆን፤ ከሁለት ቀናት በፊትም በየመን የተፈጠረው አዲስ ክስተት በርካቶችን እያነጋገረ ነው።
ክስተቱ የተፈጠረው በየመኗ አል-በይዳ ግዛት በምግተኘው የራዳአ ከተማ ሲሆን፤ በተከማዋም በሚገኝ ሆስፒታል አንድ ዐይን ያለው ህፃን መወለዱ ተሰምቷል።
በአል-ሂላል እስፔሻላይዝድ ሜዲካል ሆስፒታል የህክምና ምንጮች እንደገለፁት፤ ህጻኑ ከሁለት ቀናት የተወለደ ሲሆን፤ ከተወለደ ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ ማለፉን ጠቁመዋል።
ህፃኑ ወደ ማሞቂያ ክፍል ከተወሰደ ከሰባት ሰዓታት በኋላ ህይወቱ ማለፉን የሆስፒታሉ ምንጮች አስታውቀዋል።
የየመን ማህበራዊ አንቂ የሆነው ካሪም ዛሬይ፤ አዲስ የተወለደውን ህፃን ፎቶ በኢንተርኔት ላይ የለቀቀ ሲሆን፤ እንዲህ አይነት ነገር በግሪክ አፈ ታሪክ ውስጥ የሚገኝ ሆኖም ጥቂት እና ብርቅ መሆኑን ገልጿል።
አክሎም አለማችን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት እንደዚህ አይነት ስድስት ክስተቶችን ማስተናገዷን ገልጾ፤ የመጀመሪያው የተመዘገበው በፈረንጆቹ 1665 መሆኑንም ጠቅሷል።
በየመን የተከሰተውም አዲስ ነገር እያየን ነው ብሏል ማህበራዊ አንቂው ካሪም ዛሬይ።
ካሪም ዛሬይ በፌስቡክ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፉ ህጻኑ ከሰባት ሰአት በላይ መቆት አለመቻሉን ጠቅሶ፤ አንዳንዶች በህጻኑ አረጣጠር ላይ በህፃኑ ላይ እያደረጉ ያሉትን ነቀፋ ተቃውሟል።