በእስራኤል- ሄዝቦላህ ጦርት ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደዋል?
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ “በርካታ የእስራኤል ወታደሮችን ገድዬ ታንኮች አውድሜየለሁ” ብሏል
ሄዝቦላህ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ200 በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሷል
በእስራኤልና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል የነበረው ግጭት እየተካረረ መጥቶ አሁን ላይ ወደ ሙሉ ጦርነት ተሸጋግሯል።
እስራኤል ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ መጠኑ ከፍ ያለ የአየር ጥቃት በሊባኖስ ላይ እየፈጸመች ሲሆን፤ ከቀናት በፊት ደግሞ እግረኛ ጦሯን ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ አስገብታ እየተዋጋች ትገኛለች።
ሄዝቦላህ ለእስራኤል እየሰጠ በሚገኝው ምላሽ እስከዛሬ በቡድኑ ጥቅም ላይ ውለው የማያውቁ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ጭምር በመጠቀም በማዕከላዊ እስራኤል ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።
ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደዋል?
-የህዝቦላህ እስራኤል ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፤ ከአየር ድብደባው በተጨማሪ የፊትለፊት ውጊያም ተባብሶ ቀጥሏል።
-በዛሬው እለት በቤሩት በተፈጸመው የአየር ድብደባ የጤና ተቋማት የቴልቪዥን ጣቢያ ኢላማ ነበሩ። በጤና ተቋም ላይ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ቆሰለዋል።
-በ24 ሰዓታት ውስጥ 28 የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቀዋል።
-ሄዝቦላህ ዛሬ ወደ እስራል ጦር ይዞታዎች 20 ምድፎችንና ሮኬቶችን መተኮሱን አስታውቋል፤ ዛሬ ብቻ 17 የእስራኤል ወታሮችን መግደሉን ገልጿል።
-የእስራኤል ጦር በዛሬው እለት ተገድለዋል ስለተባሉ ወታደሮቹ እስካሁን ምንም ያላለ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት የሞቱ ወታደሮቹ ቁጥር ግን 9 ደርሰዋል ብሏል።,
-“እስራኤል በመካከለኛው የቤሩት ክፍል አዳሩን ከባድ የአየር ድብደባ ስታደርግ የነበረ ሲሆን፤ በአየር ድብደባው
ቢያንስ 6 ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒቴር አስታውቋል።
-ባለፉት 24 ሰዓታት በእስራኤል የአየር ድብደባ በሊባስ የተለያዩ አካባዎች ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ85 ሰዎች በላይ ደግሞ ቆለዋል።
-የሊባኖሱ ቡድን ሄዝቦላህ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ200 በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሷል፤ አብዛኞቹ ሮኬቶች በጋሊሌ ክልል ክፍት ቦታዎች ላይ ነው የወደቁት ተብሏል።
-በእስራኤልና በሄዝቦላህ ቡድን መካከል በደቡባዊ ሊባስ እየተደረገ ባለው ውጊያ በሁለቱም ወገን ጉዳቶችን እያስተናገዱ ነው።
-የእስራኤል ጦር በሰጠው ማብራሪያ፤ በአየር ኃይል በታገዘው የእግረኛ ጦር ውጊያበርካታ የሄዝቦላህ ተዋጊዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
-በደቡባዊ ሊባኖስ እየተካሄደ ባለው ውጊያም 8 ወታደሮቹ እንደተገደሉበትምው የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
-ሄዝቦላህ በበኩሉ በማሩን አል ራ መንድር ውስጥ ሶስት መርካታ የእስራኤል ታኮችን ማውደሙን እንዲሁም በርካታ የእስራኤል ወታሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታውቋል።
-የሊባኖሱ ቡድን ሄዝቦላህ ከፋር ኪላ በተባለ አካባ የእስራኤል ጦር መሽጉበት የነበረ ህንጻ ላይ ፈንጂ በማፈንዳት በርካታ ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉንም ገልጿል።
-ሄዝቦላህ በተዋጊዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።