ሂዝቦላህን ከ30 ዓመት በላይ የመሩት ሀሰን ናስራላህ ባሳለፍነው አርብ በእስራኤል መገደላቸው ይታወሳል
ሀሰን ነስራላህን ማን ሊተካቸው ይችላል?
እስራኤል ባሳለፍነው አርብ ሌሊት በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት የሊብኖሱ ሄዝቦላህ መሪ ሼክ ሀሰን ናስራላህን መግደሏ ይታወሳል።
የሄዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስራላህ እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸውን ባወጣው መግለጫ አረጋገጧል።
ይህን ተከትሎ የሂዝቦላህ ቀጣይ መሪ ማን ሊሆን ይችላል? የሚለው ሀሳብ የብዙዎች ትኩረት ሆኗል።
የነብዩ መሀመድ የዘር ሀረግ አላቸው የሚባሉት ሀሺም ሴፌዲን የብዙዎች ግምት ይሆናሉ ተብሏል።
ሀሺም ሰፌዲን ከናስራላህ የባሰ ደመ ሞቃት ናቸው የተባለ ሲሆን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ወታደራዊ አዛዦችን ምትክ በማስመረት ቡድኑን ወደ ቀድሞ አቋሙ ሊመልሱ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ለእስራኤል የከረረ ጥላቻ አላቸው የሚባሉት ሀሺም የሂዝቦላህ ፖለቲካ ክንፍን ሲመሩ ቆይተዋል።
የሀሰን ነስራላህ አጎት ናቸው የሚባሉት ሀሺም በፈረንጆቹ 2017 ላይ በአሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ በአሸባሪነት ተፈርጀዋል።
ከኢራን ጋር የቀደመ እና መልካም እሚባል ግንኙነት ከመኖሩ ባለፈ በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚወደዱት ነብዩ መሀመድ ጋር የስጋ ዝምድና መኖሩ ሀሺም በቀላሉ የሂዝቦላህ መሪ ተደርገው የመመረጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሚሆን ሮይተርስ ዘግቧል።
የእስልምና ትምህርቱን በኢራን ያጠናው ሀሺም ከአያቶላህ ካሚኒ ጋር ጥብቅ ግንኙነትም እንዳለው ተገልጿል።
ከ64 ዓመት በፊት በሊባኖስ የተወለደው ሀሺም ከኢራናዊያን ጋር በጋብቻ ሳይቀር የተዛመደ ሲሆን ወንድ ልጁ ከአራት ዓመት በፊት በባግዳድ በአሜሪካ የተገደለው ጀነራል ቃሲም ሱሌማኒ ልጅን አግብቷል።