በ2024 ከፍተኛ ተከፋይ የሆኑ የሀገራት መሪዎች የትኞቹ ናቸው?
በዓመት 1.6 ሚሊየን ዶላር የሚከፈላቸው የሲንጋፖር ጠ/ሚኒስትር የሚስተካከላቸው የለም ተብሏል
የመሪዎቹ ዓመታዊ ገቢ ከ1 ሚሊየን እስከ 256 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል
የተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ ምክንያቶች ለመሪዎቻቸው ከፍተኛ የሆነ ደመወዝ እንደሚከፍሉ ይታወቃል።
የሀገራቱ የሀበት መጠን እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል ሀገራቱ ለመሪዎቻው ከፍተኛ ደመወዝ እንዲከፍሉ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው።
በፖሊሲዎች፣ ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች እና ሌሎች ማካካሻዎች ለውጦች ከአመት ወደ አመት መሪዎች የሚያገኙት ገቢ እንዲለያይ እንደሚያደርግም ተነግሯል።
በመረጃው መሰረት ሲንጋፖር ከፍተኛ የሚከፈልባቸው የዓለም መሪዎችን ደረጃ ትመራለች።
በዚህም በ2024 ከፍተኛ ከተፋይ ከሆኑተ የዓለም ሀገራት መሪዎች መካከል የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ ቀዳሚው ሲሆኑ፤ በዓመት 1.6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል ተብሏል።
የሆንግ ኮንግ፣ ስዊዘርላንድ እና የአሜሪካ መሪዎች ደግሞ ከ695 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እስከ 400 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በማግኘት ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
ከፍተኛ ደመወዝ የሚከፈላቸው የሀገራት መሪዎች እና የሚያገኙት ገቢ እንደሚከተለው ቀርቧል
1 ላውረንስ ዎንግ (የሲንጋፖር) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 1.6 ሚሊየን ዶላር
2 ጆን ሊካቹ (የሆንግ ኮንግ መሪ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 695 ሺህ ዶላር
3 ቫዮላ አህመርድ (ስዊዘርላንድ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 530 ሺህ ዶላር
4 ጆ ባይደን (የአሜሪካ ፕሬዝዳንት) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 400 ሺህ ዶላር
5 አንቶኒ አልባኒዝ (አውስትራሊያ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 390 ሺህ ዶላር
6 ኦላፍ ሾልዝ (ጀርመን መሪ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 397 ሺህ ዶላር
7 ኦርሱላ ቮንዴር ሊየን (አውሮፓ ህብረት) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 364 ሺህ ዶላር
8 ካርል ንሃመር (ኦስትሪያ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 307 ሺህ ዶላር
9 ጁስቲን ቱሬዱ (ካናዳ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 292 ሺህ ዶላር
10 ክርስቶፈር ሉከሶን (ኒው ዚላንድ) የሚያገኙት ዓመታዊ ገቢ 288 ሺህ ዶላር