የብራዚሎቹ ጂሴል ቡንደቼል እና አድሪያና ሊማ በዓለማችን ካሉ አምስት ከፍተኛ ተከፋይ ሞዴሎች መካከል ናቸው
የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ሞዴሎች እነማን ናቸው?
አሜሪካዊቷ ሞዴል ጄነር ከፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ በዓለማችን ካሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሞዴሎች መካከል አንዷ ስትሆን በተጠናቀቀው 2023 ዓመት ብቻ ከማስታወቂያ ድርጅቶች 40 ሚሊዮን ዶላር እንደተከፈላት ፎርብስ ዘግቧል፡፡
ሌላኛዋ አሜሪካዊት እና የመዝናኛ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዋ ክሪሲ ቴገን 39 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ሁለተኛዋ ስትሆን ብራዚሊያዊቷ ጂሴል ቡንደቼል 33 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ክፍያ በማግኘት የዓለማችን ሶስተኛዋ ተከፋይ ሞዴል ናት፡፡
እንግሊዛዊቷ የቪክቶሪያ ሴክሬት ሞዴል ሮዚ ዋይትሌይ ደግሞ 32 ሚሊዮን ዶላር በ2023 ዓመት ገቢ ስታገኝ ሌላኛዋ የብሪታንያ ዜግነት ያላት ካራ ዴልቪንኝ 31 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ብራዚሊያዊቷ አንድሪያ ሊማ ደግሞ 30 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ክፍያ በማግኘት የዓለማችን ምርጥ ከፍተኛ ተከፋይ ሴት ሞዴሎች ተብለዋል፡፡