ሩሲያ 5 ሺህ 977 የኒውክሌር አረሮችን በመታጠቅ ቀዳሚ ስትሆን አሜሪካ ትከተላታለች
በዓለማችን ላይ ዘጠኝ ሀገራት አውዳሚውን የኒውክሌር የጦር መሳሪያ እንደታጠቁ ይታወቃል።
የኒውክሌር የጦር መሳሪያን የታጠቁ ሀገራትም ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ እስራኤል እንዲሁም በቅርቡ ራሷን ኒውክሌር የታጠቀች ሀገር አድርጋ ያወጀችው ሰሜን ኮሪያ ናቸው።
እነዚህ ሀገራት የተለያየ መጠን እና ብዛት ያለው የኒውክሌር መጠን እንደታጠቁም የአሜሪካ ሳይቲስቶች ፌዴሬሽን በፈረንጆቹ 2022 መጀመሪያ ወራት በለቀቀው መረጃ በዓለም ላይ 12 ሺህ 700 የኒውክሌር የጦር መሳሪያ እንዳሉ አስታውቋል።
ሩሲያ እና አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሺህዎች የሚቆጠር የኒውክሌር የጦር መሳሪያ አረሮቻውን ቢየስወግዱም አሁንም በዓለም ላይ ካሉት የኒውክሌር የጦር መሳሪያ አረር ውስጥ 90 በመቶውን እንደታጠቁም ነው መረጃው የሚያመለክተው።
ኒውክሌር ታጣቂ ሀገራት ያላቸው የኒውከሌር መጠን በቅደም ተከትል እንደሚከተለው ቀርቧል
1. ሩሲያ - 5 ሺህ 977
2. አሜሪካ - 5 ሺህ 428
3. ቻይና - 350
4. ፈረንሳይ - 290
5. ብሪታኒያ - 225
6. ፓኪስታን - 165
7. ህንድ - 160
8. እስራኤል - 90
9. ሰሜን ኮሪያ - 20
ከአፍሪካ ብቸኛ ኒውክሌር የነበራት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ስትሆን፤ በፈረንጆቹ 1989 ላይ በራሷ ፈቃድ መሳሪያዎችን ማስወገዷ ሚታወስ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 1990 ላይ የነበራን 6 የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎች አስወግዳለች።