የስማርት ስልኮቻችንን ደህንነት በምን መልኩ ማስጠበቅ እንችላለን?
ኦፕሬቲንግ ሲስተምና መተግበሪያዎችን ማዘመን ለስማርት ስልካችን ደህንነት ከሚጠቅሙ ተግባራት ውስጥ ይገኛሉ
ነፃ የዋይፋይ አገልግሎቶችን ባገኘን ቁጥር ከመጠቀም መቆጠብም ለስማርት ስልካችን ደህንነት ይመከራል
የመረጃ ጠላፊወች (መንታፊዎች) የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ከስማርት ስልኮቻችን ላይ መረጃ ለለመንተፍ ሲሞክሩ ይስተዋላል።
ራሳችንን ከመረጃ መንታፊዎች ለመከላከል እና የስማርት ስልካችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ይረዳሉ በሚል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነተ ኤጀንሲ (ኢንሳ) የለገሳቸውን ምክሮች እንደሚከተለው አቅርበናል።
- ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
- “ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ትላልቅ ተቋማት ላይ የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶች ከውስጥ መፈፀማቸውን ታሳቢ ማድረግ ይገባል”- ዶ/ር ሹመቴ ግዛው
ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማዘመን፡- የስልካችንን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ወቅቱን እየተበቅን ማዘመን የስማርት ስልካችንን ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል።
መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስማርት ስልካችን ላይ የምንጠቀምባቸውን መተግበሪያዎች በየወቅቱ የሚለቀቁ የክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶችን በመከታተል ማዘመንም ይመከራል።
መተግበሪያዎችን ከታማኝ ምንጮች ማውረድ፡- በስማርት ስልካችን ላይ ለተለያዩ ተግባራት የምንጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች እንደ “ጎግል ፕሌይ ስቶር እና አፕ ስቶር” ካ ከታማኝ የማውረጃ ምንጮች በማውረድ መጠቀም።
ነፃ የገመድ አልባ (ዋይ ፋይ) ኢንተርኔት አለመጠቀም፡- ለህዝብ አገልግሎት ለመስጠት ተብለው በቀረቡ ነጻ የዋይፋይ ኢንትረኔት ተጠቀመው ምስጢራዊ መረጃዎችንና ሰነዶችን አለመለዋወጥ። እንዲሁም ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት ለጥቃት ተጋላጭነትዎን ስለሚጨምር ባይንጠቀመው ይመከራል።
ስማርት ስልልካችንንና መተግበሪያዎችን መቆለፍ፡- ስማርት ስልካችንን እና በስማርት ስልካችን ላይ የሚጠቀምባቸውን እና በሦስተኛ አካል እንዲታዩ የማንፈልጋቸውን መተግበሪያዎች በአሻራ፣ በፓተርን፣ በይለፍ ቃል፣ በይለፍ ቁጥር፣ በፊት መለያ ወዘተ መቆለፍ። ለማህበራዊ ሚዲያ መጠቀምያ መተግበሪያዎችዎ የ2 ዙር ማረጋገጫ (Two-factor authentication) መጠቀም። እንዲሁም የምንጠቀምባቸ የይለፍ ቃሎች በቀላሉ የማይገመቱና በየወቅቱ የሚቀያየሩ መሆናውን ማረጋገጥ።
ፀረ-ቫይረስ መጠቀም፡- የስልካችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ከትክክለኛ ምንጭ የተገኙ ፀረ-ቫይረሶችን መጠቀም ይመከራል። ፀረ-ቫይረሶችን በስልካችን ላይ ተጭነው ልናገኝ የምንችል ሲሆን፤ በተጨማሪም ከታዋቂ የፀረ-ቫይረስ አምራች ኩባንያዎች ድረ-ገፅ፤ ከጎግል ፕሌይ ስቶር እና ከአፕ ስቶር አውርደን መጠቀምም እንችላለን።