አዲሱ ቴክኖሎጂ ከፈረንጆቹ 2050 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ተመራማሪዎች ተናግረዋል
የሞቱ ሰዎችን መንትያ መፍጠር እንደሚቻል ተመራማሪዎች ተናገሩ።
ያለንበት ዘመን ሩጫ እና ወክቢያ የበዛበት ዘመን እየሆነ ይገኛል። በዚህምክንያ ብዙዎች እንደራሳቸው አልያም ከዛም በላይ የሚወዷቸውን ሰዎች ሲያጡ በሀዘን ይጎዳሉ።
የብሪታንያው ራቭንስቦርን ዩንቨርሲቲ ግን የሞቱ ሰዎችን መንትያ ዳግም መፍጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ማግኘቱን አስታውቋል።
በዩንቨርሲቲው የኮምፒውቲንግ እና ቢዝነስ ተመራማሪው ዶክተር አጃዝ ለሜይል ኦንላየን እንዳሉት አርቲፊሺያል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሞቱ ሰዎችን መንትያ መፍጠር ይቻላል ብለዋል።
ተመራማሪው እንዳሉት ምስጋና ለአርቲፊሺያል ቴክኖሎጂ ይሁንና የሚወዱትን ሰው በሞት ቢያጡ ከአጠገብዎ እንዲሆን ዳግም ማቆየት ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ፈጠራ አማካኝነት አንድ የሚወዱት ሰው በህይወት እያለ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ፣ እንደሚያስብ፣ ደምጹ እና ሌሎች መገለጫዎቹን በቴክኖሎጂ በመውሰድ ህይቱ ሲያልፍ የነበሩትን ነገሮች ሁሉ በአርቲፊሻል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ህይወት እንዳለው ሰው ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ይቻላል ተብሏል፡፡
ይህ ፈጠራ በተለይም የፍቅር አጋራቸው ለሞተባቸው፣ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት እና ለሌሎችም የሚወዷቸውን ቤተሰብ በማጣት በሀዘን ይጎዱ ለነበሩ ሰዎች ፍቱን መሆኑንም ተመራማሪው አክለዋል፡፡
አዲሱ አርቲፊሺያል ቴክኖሎጂ የአያቶቻቸውን ተረቶች እየሰሙ ለሚያድጉ ነገር ግን ወላጆቻቸውን በሞት እያጡ ሀዘን ላይ ለሚወድቁ ህጻናት መፍትሄ እንደሚሆን በዘገባው ላይ ተገልጿል፡፡
የቴክኖሎጂ ፈጠራው በሞት ያጡት ሰውን ትክክለኛ ድምጽ፣ በተለያዩ ስሜቶች ውስጥ ሆነው ያወጧቸው የነበሩ ድምጾችን ሳይቀር ልክ በህይወት ያሉ ያህል እንዲነጋገሩ ማድረግ ያስችላልም ተብሏል፡፡
ይሁንና ይህ ቴክኖሎጂ ከፈረንጆቹ 2050 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ እንደሚውል ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡